Friday, October 4, 2019

የአርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

➽ቻን 2020| ለሩዋንዳው የመልስ ጨዋታ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል

ግብ ጠባቂዎች(3)፡ ምንተስኖት አሎ (መከላከያ)፣ ጀማል ጣሰው ( ፋሲል ከነማ)፡ ለዓለም ብርሃኑ (ቅ/ጊዮርጊስ)


ተከላካዮች(8)፡ አስቻለው ታመነ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ደስታ ደሙ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (መከላከያ)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጌቱ ኃ/ማሪያም (ሰበታ ከተማ)፣ መሳይ ጳውሎስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረመዳን የሱፍ (ስሁል ሽረ)


አማካዮች(6)፡ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅ/ጊዮርጊስ)፤ ዮናስ በርታ(አዳማ ከተማ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፡ ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)


አጥቂዎች(7) ፡ አስቻለው ግርማ (ሰበታ ከተማ)፣ ፉአድ
ፈረጃ (አዳማ ከተማ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣
አማኑኤል ገ/ሚካኤል (መቐለ 70 እንድርታ)፣ ሙጂብ
ቃሲም (ፋሲል ከነማ)፣ ፍቃዱ ዓለሙ (መከላከያ)፣ አዲስ
ግደይ (ሲዳማ ቡና)
(Soccer Ethiopia)


የውጭ ዜናዎች

➽የአሁኑ ማን ዩናይትድ ባለፉት አስርት አመታት ከታዩ ቡድኖች ሁሉ ደካማው መሆኑን የቀድሞው ተጨዋች ማይክል ኦውን ተናገረ።ኦውን ክለቡ በዚህ አያያዙ ምርጥ ስድስት ውስጥም ሊገባ አይችልም ሲል ነው የተናገረው።አሌክሲስ ሳንቼዝ ፥ ሮሜሮ ሉካኩ እና ሄሬራን ቀያይ ሰይጣኖቹ መልቀቃቸውም ስህተትህ መሆኑን ገልጿል።የቀድሞው ታላቅነቱን እያጣ ያለው ዩናይትድ ከዚህ በኋላ ለተከታታይ አመታት ሊቸገር ይችላልም ብሏል።
(BT Sport)





➽ማን ዩናይትድ በጥር ወር የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት የአጥቂ ስፍራ ተጨዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋል።እንግሊዛዊው የበርንመዝ አጥቂ ካሉም ዊልሰን እና ክሮሺያዊው የጁቬንትስ አጥቂ ማሪዮ ማንዙኪች ደግሞ ዋነኛ ዕቅዶቹ ናቸው፡፡
(Sky Sports)




➽የዴንማርካዊው የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ወኪል በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ስፔን እንደሚጓዝ ይጠበቃል።ወኪሉ ጉዞውን የሚያደርገው ከሪያል ማድሪድ የበላይ አመራሮች ጋር ለመወያየት ነው፡፡ኤሪክሰን ስፐርስን ይለቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጨዋቾች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው።
(Star)





➽ማውሩዚዮ ሳሪ በቼልሲ ሳሉ ቁልፍ ተጨዋቻቸው የነበረውን ብራዚላዊውን ዊሊያን ወደ ጁቬንትስ ለማምጣት ፍላጎት አላቸው።ፍራንክ ላምፓርድ ግን የ31 አመቱን አጥቂ በስታንፎርድ ብሪጅ ለማቆየት አዲስ ኮንትራት እንደሚቀርብለት ተናግሯል።
(Calciomercato)




➽ንብረትነቱ የሪያል ማድሪድ ሆኖ ሪያል ሶሴዳድ በውሰት እየተጫወተ ያለውን የ20 አመቱን ኖርዌያዊ አጥቂ ማርቲን ኦዴጋርድ ሎስብላንኮዎቹ ወደ በርናቢዮ ሊመልሱት ነው።በአንድ ወቅት አለምን ሲያነጋግር የነበረው ኦዴጋርድ በሊቨርፑል እና ማን ዩናይትድ ይፈለጋል፡፡
(Goal)




➽ጣሊያናዊው አንጋፋ አሰልጣኝ ፋቢዮ ካፔሎ በአንድ ወቅት በጁቬንትስ ሳሉ አርጀንቲናዊውን ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንዳልተሳካላቸው ተናገሩ።
(Sky Sports Italia, via Mail)



➽ኢንተር ሚላን በውሰት ከማን ዩናይትድ ያመጣውን ቺሊያዊውን ኮከብ አሌክሲስ ሳንቼዝ  በቋሚነት የማስፈረም እቅድ አለው።ነገር ግን ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር በውሰት ሲወስዱት ፍላጎት ካላቸው በክለቡ ያማስቀረትን ውል አልተዋዋሉም ፥ በዚህም ምክንያት በሌሎች ክለቦች እንዳይነጠቁ ይሰጋሉ።
(Calciomercato)



➽ሪያል ማድሪድ ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከአመት በፊት ከቼልሲ ከተሰናበተ በኋላ ለመሾም ፍላጎት ነበረው።ኮንቴ አሁን በኢንተር ሚላን አስደናቂ አመት እያሳለፈ መሆኑ ይታወቃል።
(Fichajes.net, via Calciomercato)





➽ኡናይ ኤምሬ ምንጊዜም ቋሚ አስራ አንድ ውስጥ የሚያስገቡት ተጨዋች የተሻለ ይሰራል የሚሉት እና መሰለፍ ይገባዋል የሚሉትን እንደሆነ ተናገሩ፡፡ኤምሬ ይህንን ያሉት የክለቡ ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ የሆነው ኦዚል ለምን ብዙ ዕድል እንደማይሰጠው ሲጠየቁ ነው።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ኦዚል በቋሚነት ለመሰለፍ ብቃቱን ማሻሻል እንዳለበት ተናግረዋል።
(Goal)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...