Thursday, October 3, 2019

የሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

⇢ባህር ዳር ከተማ የግብ ጠባቂውን
ውል አራዝሟል
የ25 ዓመቱ ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ ሃሪስተን ሄሱ ከጣናው
ሞገዶቹ ጋር ለመቆየት ውሉን ለአንድ ዓመት አራዝሟል።
አምና ከኢትዮጵያ ቡና ወደ ባህር ዳር ከተማ በመዘዋወር
የ2010 የውድድር አመትን በኢትዮጵያ ያሳለፈው ተጨዋቹ
በውድድር ዓመት ጅማሮ ላይ በቋሚነት መሰለፍ ሳይችል
መቅረቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቀስ በቀስ የቋሚነት ቦታን
ከምንተስኖት አሎ እየወሰደ ጥሩ ግልጋሎት አበርክቷል።
በ2008 ኤ ኤስ ድራጎንስን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው ተጨዋቹ ለሁለት ዓመታት በቡናማዎቹ ቤት ቆይቶ አምና ወደ ባህርዳር ማቅናቱ ይታወሳል።
(Soccer Ethiopia)


የባህር ማዶ ዜናዎች

⇢ማን ዩናይትድ የሌስተር ሲቲውን የጨዋታ ቀማሪ ጄምስ ማዲሰን ለማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት አለው።ቀያይ ሰይጣኖቹ የ22 አመቱን ተጨዋች ባለፈው የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጥረት አድርገው እንዳልተሳካላቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን £80ሚ. ነው ያሰናዱት።
(Mail)





⇢በባየርን ሙኒክ ሰባት ግብ ከተቆጠረበት በኋላ ብዙ አሉታዊ አስተያየቶች እየተሰጡበት ያለው ቶተንሃም ቁልፍ ተጨዋቾቹ ሊለቁበት እንደሚችሉ እየተነገረ ነው።ከነዚህም ውስጥ የ26 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሃሪ ኬን ዋነኛው ነው።
(Times -subscription required)




⇢የቀድሞው የጁቬንትስ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ በቀጣይ ክረምት ወደ አሰልጣኝነት እንደሚመለሱ ታውቋል።አሌግሪ ለአንድ አመት ገደማ ከአሰልጣኝነት ርቀው ነው የሚመለሱት።
(Sun)




⇢የጁቬንትሱ አሰልጣኝ ማውሩዚዮ ሳሪ በቼልሲ ሳሉ ቁልፍ ተጨዋቻቸው የነበረውን ድንቁን ፈረንሳዊ አማካይ ንጎሎ ካንቴ ወደ ክለባቸው ለማምጣት ፍላጎት አላቸው።ጁቬንቱስ ይህንን ዝውውር ከዳር ለማድረስ £70ሚ. ያስፈልገዋል።
(Mail)




⇢ኦሊጉናር ሶል ሻየር በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሶስት የአጥቂ ስፍራ ተጨዋቾችን የማስፈረም እቅድ ያለው ሲሆን ከነዚህም መሀከል ዋነኛው የ22 አመቱ ፈረንሳዊ የባርሴሎና አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ ነው።
(Manchester Evening News)




⇢እንግሊዛዊው የ24 አመት የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ራሂም ስተርሊንግ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ስብስባቸው ሻምፒየንስ ሊግ ማንሳቱ እንደማይቀር ተናግሮ እስከዛ ግን የቡድን አጋሮቹ በትዕግስት እና በትጋት መስራት እንዳለባቸው አስተያየቱን ሰጥቷል።
(Mirror)




⇢የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የክለቡ ሪከርድ በሆነ £72ሚ. ከተዘዋወረ በኋላ እምብዛም አመርቂ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለሆነው ኒኮላስ ፔፔ የሚመጣበትን ጫና መቋቋም አለበት አሉ።አሰልጣኙ ኮዲቫራዊው ኢንተርናሽናል በስነ ልቦና ደረጃ መጠንከር እንዳለበትም ተናግረዋል።
(Mirror)




⇢ቼልሲ የሞናኮውን ሴንተር ባክ ቤኖት ባዲያሺ የዝውውር እገዳው ከተነሳለት ማስፈረም ይፈልጋል።ፍራንክ ላምፓርድ የ18 አመቱን ፈረንሳዊ በጥብቅ ይሻዋል።
(Le 10 Sport, via The Sun)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...