Wednesday, October 2, 2019

የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


የሀገር ውስጥ ዜናዎች

➽የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ወቅታዊ እግርኳሳዊ ጉዳዮች ዙርያ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር
ለመነጋገር ዛሬ የተጠራው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀረ።
የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥቅምት 1 ከሚካሄደው የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ በፊት በሊግ አደረጃጀት የአሰራርና የአመራር ችግሮች የሚዳስስና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ጥናት ለባለድርሻ አካላት ለማቅረብ ጥሪ እንዲደረግለት ለኢትዮጵያ እግርኳስ
ፌዴሬሽን ደብዳቤ ማስገባቱ ይታወቃል።
ዛሬ 04:00 ፌዴሬሽኑ አዲስ በገዛው ህንፃ ላይ በጥናቱ አቀራረብ ዙርያ ለመነጋገር በተያዘው ቀጠሮ መሠረት የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንትን ጨምሮ የሥራ አስፈፃሚ አባለት እና ጥናት አቅራቢው ባለሙያ በሰዓቱ ቢገኙም የፌዴሬሽኑ አመራሮች ለሌላ አስቸኳይ ስብሰባ ሄደናል በማለታቸው ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል።
(Soccer Ethiopia)




➽በጅማ አባጅፋር ጥሩ ቆይታ የነበረው ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ባህር ዳር ከተማን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፡፡
የ26 ዓመቱ አጥቂ በ2011 የውድድር ዘመን የሞሮኮውን ራፒድ ኦውድን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በጅማ አባጅፋር በግሉ የተሳካ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ እና በአፍሪካ ውድድር ጥሩ እንቅስቃሴ ከማሳየቱ በተጨማሪ ወሳኝ ጎሎችንም ማስቆጠር ችሏል።
በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት የጣና ሞገዶቹ ከቀድሞው ኦሊምፒክ ኮሪብጋ፣ ራቻድ ቤርኖውሲ እና ኤኤስ ፖሊስ አጥቂ በተጨማሪ ከቀናት በፊት የከፍተኛ ሉጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነውን አጥቂ ስንታየው መንግስቱን ማስፈረማቸውም ይታወሳል፡፡
(Soccer Ethiopia)


የባህር ማዶ ዜናዎች


➽ባርሴሎና ብራዚላዊውን የ31 አመት የሰማያዊዎቹ አጥቂ ዊሊያን ለማዘዋወር ከወዲሁ አቅዶ እየሰራ ነው።ተጨዋቹ ክረምት ውሉ የሚጠናቀቅ ሲሆን ፥ ቼልሲ ከወዲሁ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለትም ነው።
(Mundo Deportivo, via Express)




ማንቸስተር ዩናይትድ የሊዮኑን ፈረንሳዊ የ23 አመት አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ እና የኒውካስትል ዩናይትዱን የ21 አመት አማካይ ሲን ሎንግስታፍ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።
(Star)




አርሰናል ጀርመናዊውን አማካይ ሜሱት ኦዚልን በጥር ወር የዝውውር መስኮት መሸጥ ይፈልጋል።የዚህ ምክንያት ደግሞ የተጨዋቹን ሳምንታዊ ደሞዝ £350,000 ለማስቀረት ነው።
(Mail)




የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የሰሜን ለንደኑን ክለብ ከለቀቁ በኋላ ብዙ ክለቦች አስደናቂ ፕሮፖዛል እንዳቀረቡላቸው ተናግረዋል።የ69 አመቱ ፈረንሳዊ ሰው አዲስ ክለብ ሊይዙ እንደሚችሉም ፍንጭ ሰጥተዋል።
(Mirror)




ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዳናሩማ ኤሲ ሚላን ያቀረበለትን በአመት  £5.3ሚሊየን የሚያስገኝለትን ኮንትራት ውድቅ አድርጓል።
(Corriere dello Sport, via Sun)




የቶተንሀም ተጨዋቾች አሰልጣኛቸው ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ በቅርቡ እንደሚሰናበት እንደሚያምኑ ተነግሯል።አርጀንቲናዊው ድንቅ አሰልጣኝ ኦሊ ጉናር ሶልሻየርን በመተካት ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ እንደሚያቀና በስፋት እየተዘገበ ነው።
(Sun on Sunday)





ፖቼቲንሆ ቶተንሃምን ይለቃል የሚለው ዜና ሚዛን እየደፋ መምጣቱን ተከትሎ ስፐርስ አርጀንቲናዊውን ሰው የሚተካለትን እየፈለገ ይገኛል።የሰሜን ለንደኑ ክለብ የመጀመሪያ ምርጫም የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት መሆኑ ታውቋል።
(Star Sunday)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...