Friday, September 27, 2019

ማን ዩናይትድ ፖቼቲንሆን በአሰልጣኝነት ለመቅጠር እየሰራ ነው

ማን ዩናይትድ ፖቼቲንሆን በአሰልጣኝነት ለመቅጠር እየሰራ ነው

                        አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



በኦሊ ጉናር ሶልሻየር ስር ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማንችስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን የስፐርስ አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ለመቅጠር እየሰራ ነው።

ባሳለፍነው አመት የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው ፖቼቲንሆ ለረዥም ጊዜ በቀያይ ሰይጣኖቹ ሲፈለግ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተለይ በዚህ ሰዓት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ሶልሻየር እንዲተካላቸው የእነ ኢድ ውድ ዋርድ አስተዳደር ከፍተኛ ፍላጎት አለው።

እንደ ዘ ሰን ዘገባ ከሆነ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ በስፐርስ የሚያቆይ ኮንትራት ስላለውም ማን ዩናይትድ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማምጣት ከፈለገ የውል ማፍረሻውን £32 ሚሊየን ($39.4m)  መክፈል ይጠበቅበታል።


ሶልሻየር በዕለተ ሰኞ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኦልድ ትራፎርድ  ላይ ማን ዩናይትድ አርሰናልን በሚያስተናግድበት ጨዋታ  ድል ካልቀናው በቲያትር ኦፍ ድሪምስ ያለው እህል ውሃ ያበቃል እየተባለም ነው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...