ስፔን ላሊጋ
⇒ሌጋኔስ ከ አትሌቲክ ቢላባኦ - 2:00
⇒ማዮካ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ - 2:00
⇒ቫሌንሲያ ከ ሄታፌ -3:00
⇒ሪያል ማድሪድ ከ ኦሳሱና - 4:00
ጣሊያን ሴሪያ
⇒ሮማ ከ አታላንታ - 2:00
⇒ፊዮረንቲና ከ ሳምፕዶሪያ - 4:00
⇒ጄኖዋ ከ ቦሎኛ - 4:00
⇒ኢንተር ሚላን ከ ላዚዮ -4:00
⇒ፓርማ ከ ሳሱሎ - 4:00
⇒ናፖሊ ከ ካጊላሪ - 4:00
⇒ስፓል ከ ሊቼ - 4:00
ሪያል ማድሪድ በአሁኑ ሰዓት በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ድንቅ ተጨዋቾች አንዱ የሆነውን የማንቸስተር ሲቲውን የ24 አመት አጥቂ ራሂም ስተርሊንግ ለማዘዋወር ከአሁኑ አቅዷል።ስተርሊንግ በያዝነው አዲሱ አመት በአጠቃላይ ለክለብ እና ለሀገሩ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሰባት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
ሊቨርፑል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ካቀዳቸው ተጨዋቾች ውስጥ የሌስተር ሲቲው እንግሊዛዊ አማካይ ጄምስ ማዲሰን አንዱ መሆኑ ተገልፇል።
ሌላ ከሊቨርፑል ጋር በተያያዘ ዜና ቀያዮቹ ከአለም አቀፉ የትጥቅ አቅራቢ ናይክ ጋር ከቀጣዩ አመት ጀምሮ አብረው ለመስራት እየተደራደሩ ሲሆን ከስምምነት ላይ ለመድረስም ጥቂት ነገር ብቻ ቀርቷል።ስምምነቱ የሚሰምር ከሆነ ሊቨርፑል ከሁሉም ክለቦች በላይ ከፍተኛ ተከፋይ ይሆናል ተብሏል።
ቀውስ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ሲከፈት በርካታ ተጨዋቾችን እንደሚያስፈርም እየተነገረ ነው።ከነዚህ ተጨዋቾችም መሀከል እንግሊዛዊው የኒውካስትል አማካይ ሲን ሎንግስታፍ እና የ ራ.ቢ ሳልዝቡርጉ የ19 አመት ኖርዌያዊ አጥቂ ኤርሊንግ ብራውት ዋነኞቹ ናቸው።
በሌላ ዜና ከወደ ማንቸስተር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚሉት ኦሊጉናር ሲልሻየር ከቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ሊሰናበት ነው እየተባለ ነው።
የቼልሲው ብራዚላዊ አጥቂ ዊሊያን በጁቬንትስ እየተፈለገ ነው።ውሉ በክረምት የሚገባደደው የ31 አመት ተጨዋች አዲስ ውል የማይፈርም ከሆነ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት በፍቃዱ ወደ ፈለገበት ክለብ እንዲሄድ የቦስማን ሕግ ይፈቅድለታል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት የ33 አመቱን ክሮኤሽያዊ የጁቬንትስ አጥቂ ማርዮ ማንዙኪች እና የ22 አመቱ ፈረንሳዊ የባርሴሎና አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ ማስፈረም ይፈልጋል።
የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሊቨርፑልን ሲለቅ በአሁኑ ሰዓት ሬንጀርስን እያሰለጠነ ያለው የቀድሞ የቀያዮቹ ሌጀንድ ስቴቨን ዤራርድ እሱን እንደሚተካ ተናገረ።
የአርሰናሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቪናይ ቬንካትሻም ክለባቸው በቀጣዩ የዝውውር መስኮት እምብዛም ተሳታፊ እንደማይሆን ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment