ቅድመ ጨዋታ ዕይታ | ናፖሊ ከ ሊቨርፑል
ዛሬ ተወዳጁ እና ታላቁ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲጀመር ፥ በርከት ያሉ መርሀ ግብሮችም ይከናወናሉ።ከነዚህ መርሃ ግብሮች መሀከል ደግሞ በኔፕልስ ናፖሊን ከአምናው ሻምፒዮን ሊቨርፑል የሚያገናኘው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።እኛም እዚህ ጨዋታ ላይ ትኩረት አድርገናል …… ሰናይ ንባብ!
የቡድን ዜናዎች
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከ ኒውካስትል ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ቤልጄሚያዊው አጥቂ ዲቮክ ኦሪጊ ትናንት ወደ ጣሊያን ከተጓዙት ሀያ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም።ከሱ በተጨማሪ አሊሰን ቤከር ፥ ናቢ ኬይታ ፥ ናትናኤል ክላይንም በሊቨርፑል በኩል በጉዳት ምክንያት ከዚህ ጨዋታ ውጪ ሲሆኑ አንዲ ሮበርትሰንም በፊትነስ ምክንያት ይህ ጨዋታ ሊያመልጠው ይችላል ተብሏል።
ከባለፈው ወር ጀምሮ ጉዳት ላይ የሰነበተው አርካዙኤዝ ሜሊክ በናፖሊ በኩል ከዚህ ጨዋታ ውጪ የሚሆን ሲሆን በቅድመ ውድድር ዝግጅት ሁለቱ ክለቦች ሲገናኙ ግብ አስቆጥሮ የነበረው እና ባሳለፍነው ሳምንት ከጉዳት አገግሞ ልምምድ መስራት የጀመረው ሎሬንዞ ኢንሴኚ ለዚህ ጨዋታ ብቁ ነው።
የ 'Opta' ቁጥራዊ ዕውነታዎች
ዛሬ ናፖሊ እና ሊቨርፑል በአውሮፓ ውድድር የሚገናኙት ለአምስተኛ ጊዜ ነው።በ2011 ዩሮፓ ሊግ እና ባሳለፍነው አመት የሻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ በአንድ ምድብ ውስጥ ነበሩ።
ሊቨርፑል ባለፈው አመት ከሜዳው ውጪ በናፖሊ 1-0 ሲሸነፍ አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ አላደረገም ነበር።ይህም ቀያዮቹ ባለፉት 74 ጨዋታዎች ካደረጉት ጨዋታ ደካማው ነበር።
ናፖሊ በአውሮፓ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው፥እሱም ባሳለፍነው አመት ሊቨርፑልን የረታበት ነበር።በአምስቱ ሲሸነፍ በሶስቱ ጨዋታ ደግሞ ግብ ሳያስቆጥር ነበር የተሸነፈው።
ባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ አመታት ሊቨርፑል 65 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን 15 ጨዋታዎችንም ማሸነፍ ችሏል።በዚህም ከየትኛውም ክለብ በላይ ስኬታማው ነው።
የሊቨርፑሉ ሳዲዮ ማኔ በ24 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች 14 ግቦችን አስቆጥሯል።ዛሬ አንድ ግብ የሚያስቆጥር ከሆነ ዲዲዬ ድሮግባ ይዞት የነበረውን አፍሪካዊ ተጨዋች ሆኖ በ25 ጨዋታዎች 15 ግብ የማስቆጠር ሪከርድ የሚጋራ ይሆናል።ከአንድ ግብ በላይ ካስቆጠረ ደግሞ ሪከርዱ የግሉ ይሆናል።
No comments:
Post a Comment