Thursday, September 19, 2019

"ሀዛርድ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለበት ወቅት ትክክለኛ አይደለም" ሪዮ ፈርዲናንድ

"ሀዛርድ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለበት ወቅት ትክክለኛ አይደለም" ሪዮ ፈርዲናንድ


ቤልጄሚያዊው ኮከብ ኤድን ሀዛርድ ትናንት በሎስ ብላንኮዎቹ ማሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት ጨዋታውን ሲያደርግ ቡድኑ በፔዤ 3ለ0 ተሸንፏል፡፡
በቀድሞው የቼልሲ ተጨዋች ዙሪያም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን የቀድሞው የማን ዩናይትድ ሌጀንድ ሪዮ ፈርዲናንድም ስለ ሀዛርድ ሲናገር ልጁ ሎስ ብላንኮዎቹን የተቀላቀለው የስፔኑ ክለብ እጅግ በተዳከመበት ወቅት ነው ብሏል።

ከBT Sports ጋር ቆይታ ያደረገው ፈርዲናንድ

"ወደ አዲስ ክለብ ስትቀላቀል ፥ በተለይ እንደ ማድሪድ ወዳ አለ ትልቅ ክለብ ፥ ኳስን እንደ ፈለክ የመጫወት ነፃነት ሊሰጥህ ይገባል።
በትሬኒንግ ላይ በተወሰነ ደረጃ እንደሚሰራ እገምታለሁ ፥በነጥብ ጨዋትዎችም ግን ይህንን መድገም ያሻል።
ወደ ክለቡ የተቀላቀለበት ወቅት ትክክለኛ አይመስለኝም።"  ብሏል።


በተጨማሪም ትናንት ጨዋታውን ከፈርዲናንድ ጋር ሲተነትን የነበረው ፒተር ክሮች
"ሀዛርድ በቼልሲ እያለ አለም ላይ ካሉ ምርጥ አምስት ተጨዋቾች አንዱ ነበር ፥ ዛሬ ያየነው ሀዛርድ ግን እጅግ ደካማ ነው።
በቼልሲ እያለ የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ነበር ፥ የቡድን አጋሮቹም ከየትኛውም ቦታ በተደጋጋሚ ኳስን ያቀብሉት ነበር።በማድሪድ ግን ይህ እየሆነ አይደለም።" ብሏል።


ሀዛርድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከቼልሲ ወደ ሪያል ማድሪድ €100 million (£88m/$112m) መዘዋወሩ አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...