Wednesday, August 21, 2019

"በቀጣዩ አመት ጫማ ልሰቅል እችላለሁ" ሮናልዶ

"በቀጣዩ አመት ጫማ ልሰቅል እችላለሁ" ሮናልዶ


ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለጊዜው መች እግር ኳስ ማቆም እንዳለበት ያልወሰነ ቢሆንም ፥ ምናልባትም ግን በቀጣዩ አመት ሊሆን እንደሚችል ተናገረ።

የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሮናልዶ ከTVI ጋር በነበረው ቆይታ

"መቼ እግር ኳስ እንደማቆም አልወሰንኩም።ምናልባትም በቀጣዩ አመት ሊሆን ይችላል ፥ ነገር ግን እሰከ 40 አመቴ የመጫወት ብቃቱ አለኝ።ብቻ መቼ እንደሚሆን አላውቅም።አሁን ያለውን ጊዜ በጥሩ መልኩ ማሳለፍን ነው የምፈልገው።" ብሏል።

ስለ ሪከርዶቹ ተጠይቆም

"በኔ ደረጃ ትልቅ ሪከርድ ያላቸው ተጨዋቾች አሉ? አይመስለኝም።በኔ ደረጃ ሪከርዶችን የሰበር እግር ኳስ ተጨዋች የለም።" ብሏል


የ34 አመቱ ፖርቱጋላዊ ባሳለፍነው አመት አሮጊቷን ከተቀላቀለ አንስቶ  በቱሪን በሁሉም የውድድር አይነቶች 43 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን 28 ግቦችንም ከመረብ አሳርፏል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...