Friday, August 9, 2019

የዕለተ አርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች



ኤቨርተኖች ናይጄሪያዊውን አሌክስ ኢዮቢን ከአርሰናል በ£40m አስፈርመውታል በጉዲሰን ፓርክም ለአምስት አመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል





አርሰናል የ32 አመቱን ብራዚላዊውን ተከላካይ ዴቪድ ልዊዝን በ£8m ከቸልሲ አስፈርመውታል በአርሰናልም 23 ቁጥር መለያን ይለብሳል




ሼፍልድ ዩናይትዶች ሞ ቤሲክን በአንድ አመት የውሰት ውል ከኤቨርተን አስፈርመውታል





ሌስተር ሲቲ ዴኒስ ፕሪቲን ከሳምፕዶሪያ በ£18m አስፈርመውታል በኪንግፓወርም አምስት አመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል




አርሰናል ኬረን ቴርኒን ከሴልቲክ በ£25m አስፈርመውታል በአርሰናልም የ3 ቁጥር መለያን ሚያደርግ ይሆናል




ማንችስተር ሲቲዎች የደርቢ ካውንቲ ግብ ጠባቂውን ስኮት ካርሰንን በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውታል




ቶተንሀም ጆቫኒ ሌሴልሲዮን በአንድ አመት የውሰት ውል ከሪያል ቤትስ አስፈርመውታል ይህ ዝውውር በቀጣይ ክረምት ቶተንሀም ለሪያል ቤትስ £60m በመክፈል ቋሚ ያደርገዋል




ሀደርስፊልድ የቸልሲውን ወጣት አማካይ ተጨዋች ትሬቮህ ቻሌቦህን በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውታል



ብራይተን ሆብ አልቢዮኖች አሮን ሞይን ከሀደርስፊልድ በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውታል




ኢንተርሚላን ሮሜሉ ሉካኩን ከዩናይትድ £65m + £13m አስፈርመውታል በኢንተርም የማውሮ ኢካርዲን 9 ቁጥር ይለብሳል




ኒውካስትሎች የቀድሞ ልጃቸውን አንዲ ካሮልን በነፃ አስፈርመውታል በኒውካስትል የአንድ አመት ኮንትራት ሲሰጠው ብቃቱ እየታየ ኮንትራቱ ይራዘምለታል




ቶተንሀም ሪያን ሴሴኞን ከፉልሀም በ£25m አስፈርመውታል በቶተንሀምም የስድስት አመት ኮንትራት ተፈራርሟል



ዋትፎርድ እስማኤል ሳሪን ከሬንስ በ£35m ቦነስ አስፈርመውታል በዋትፎርድም ለአምስት አመት ለመቆየት ተስማምቷል




ዌስትብሮሞች ቻርሊ ኦስቲንን ከሳውዛንብተን በ£4m አስፈርመውታል ኦስቲን በዌስትብሮም የሁለት አመት ኮንትራት ፈርሟል




ስቶክ ሲቲ ካሜሮን ካርተር ቪተርስን ከቶተንሀም በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውታል



ጀርመናዊው ኤልካይ ጎንዶጋን በማንችስተር ሲቲ እስከ 2023 የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል




ሀል ሲቲ ማቲው ፔንግተን የተባለ ተከላካይ በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...