Thursday, August 8, 2019
የሀሙስ አመሻሽ ስፖርታዊ ዜናዎች
በክረምቱ ሳውዛንብተንን ይለቃል ሲባል የነበረው የመስመር አጥቂው ናታን ሬድሞንድ እዛው መቆየትን መርጧል ሳውዛንብተን ያቀረበለትን ኮንትራት ማራዘሚያ በመቀበል እስከ 2023 የሚያቆየውን አዲስ ውል ተፈራርሟል
ኒውካስትል ዩናይትዶች ኢሚል ክራፍትን ከአሚንስ አስፈርመዋል ኒውካስትሎች ለተጨዋቹ £5m የከፈሉ ሲሆን የአራት አመት ኮንትራትም ፈርሟል
አዲስ አዳጊዎቹ አስቶንቪላዎች የአማካያቸውን ጆን ምስጊንን ኮንትራት አራዝመዋል ተጨዋቹ እስከ 2024 የሚያቆየውን ውል ነው የፈረመው
ዩናይትዶች ማርከስ ሮሆን በውሰት ለመስጠት አልያም እስከ £28m ለኤቨርተን ለመሸጥ በንግግር ላይ ናቸው ተጫዋቹም በቂ የመሰለፍ እድል ማግኘት ይፈልጋል ዝውውሩን ለመጨረስ ዛሬ ጠዋት ከወኪሉ ጋር ካሪንግተን እንደተገኘ ተረጋግጧል
ዌስትብሮም እና ብሪስቶል ሲቲ የሳውዛንብተኑን አጥቂ ቻርሊ ኦስቲንን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ አሁን ከሰአት እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ዌስትብሮም እና ሳውዛንብተን ከስምምነት ደርሰዋል
ዌስትሀም ዩናይትድ ተጨማሪ አጥቂ አስፈርሟል ዌስትሀሞች ከባዜል አልቢያን አጄቲን ነው በ£8m ማስፈረም የቻሉት
የአርሰናሉ ተስፈኛ ኤዲ ኒኪታ በአንድ አመት የውሰት ውል ሊድስን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል
ማንችስተር ሲቲዎች ስቶክ ካርሰንን የኤደርሰን ሞራየስ እና የክላውዲዮ ብራቮ ተጠባባቂ ለማድረግ ከደርቢ ካውንቲ በውሰት ሊያስፈርሙት ተቃርቧል
አርሰናሎች ዴቪድ ልዊዝን ከቸልሲ በ£8m ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል እንዲሁም ኬራን ቴርኒን ከሴልቲክ በ£25m ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ሁለቱም ተጨዋቾች ዛሬ በይፋ እንደሚቀላቀሉ ተሰምቷል
ቶተንሀም እና ፉልሀም በሪያን ሴሴኞል ዝውውር ላይ በአብዛኛው ከስምምነት ደርሰዋል ቶተንሀም ለልጁ እስከ £25m የሚከፍል ሲሆን አሁን ላይ ለሜዲካል ለንደን እንደደረሰ ተሰምቷል
ማንችስተር ሲቲ ጃኦ ካንሴሎን ከጁቬንቱስ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል በተቃራኒውም ጁቬንቱሶች የሲቲውን ዳኔሎን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል
ክሪስታል ፓላስ ኤቨርተኖች በዊልፍሬድ ዘሀ ዝውውር ላይ ከገንዘብ በተጨማሪ ማካርቲን እንጨምርላቹ ቢባሉም ዝውውሩን ውድቅ በማድረግ ማካርቲን ብቻውን በ£8m ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል
የቀድሞ የባርሴሎና እና የስቶክ ሲቲ ኮከብ ቦያን ኪርኪች በመጨረሻም ሞንትሪያል ኢምፓክትን ተቀላቅሏል
ቶተንሀሞች በጆቫኒ ሌሴልሲዮ ዝውውር ጉዳይ ከሪያል ቤቲስ ጋር ከስምምነት ደርሰዋል ቶተንሀሞች ለተጨዋቹ £55m የሚከፍሉ ይሆናል
የሳውዝንብተኑ የመስመር ተጨዋች ጆን ሲምስ ኒውዮርክ ሬድቡልን በአንድ አመት የውሰት ውል ተቀላቅሏል
ቶተንሃሞች በመጨረሻ ሰዓት ብሩኖ ፈርናንዴዝን ከማስፈረም ዉድድር ዉስጥ እራሳቸዉን አግለዋል ዩናይትዶች ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ
ቶትንሀም ሆትስፐር እና ጁቬንቱስ በ25 አመቱ ተጨዋች ፓብሎ ዲባላ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ተቃርበዋል ዝውውሩም በጥቂት ሰአታብ ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ BBC አስነብቧል
ሪያል ማድሪድ ኔይማርን ከፒኤስጂ ለማስፈረም ሉካ ሞድሪች እና £110m አቅርበዋል
ዩናይትድ እና ኢንተር ሚላን በሮሜሉ ሉካኩ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ደረሱ ኢንተሮች ለተጨዋቹ እስከ £80m ድረስ እንደሚያወጡ ተሰምቷል ሉካኩ ትናንት ምሽት ወደ ሚላን ከተማ ገብቷል
ፊሊፔ ኩቲንሆ ወደ አርሰናል መዘዋወር እንደሚፈልግ እና በወኪሉ በኩል ለአርሰናል ጥያቄ እንዳቀረቡ ቢነገርም የአርሰናል ሰዎች ዝውውሩን ሳይቀበሉት ቀርተዋል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment