Wednesday, August 7, 2019

የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


እንደ sky italia ዘገባ ከሆነ ዩናይትዶች ሮሜሎ ሉካኮን ለኢንተር ሚላን መሸጣቸው አይቀሬ መሆኑን ተከትሎ ከውል ነፃ የሆነውን የቶትንሃሙን አጥቂ Fernando Llorente ለማዘዋወር ከተጫዋቹ ጋር በግል ጥቅማጥቅም ጉዳይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል




አርሰናሎች ለአርቢ ላይብዢክ ያቀረበው የ£55m ጥያቄ ውድቅ ተደርጎባቸዋል ሌብዢኮች ለተጨዋቹ እስከ 92ሚዩ ይፈልጋሉ ይህንንም ተከትሎ አርሰናሎች ወደ ሌላ ተከላካይ ፊታቸውን ያዞራሉ




የአንቷን ግሪዝማነን ኑካምፕ መድረስ ቦታ የሚያሳጣው ብራዚላዊው ኮከብ ፊሊፔ ኮቲንዮ በውሰት ብሉግራናዎቹን ለመልቀቅ የመውጫ በር ላይ ቆሟል የሰሜን ለንደሩ ክለቡ(የቶትንሃም አሰልጣኝ ማውርስዮ ፖቸቲኖ ለፊሊፔ ኮቲንዮ ደውሎ እኛን ተቀላቀል ብሎታል ዝውውሩ ግን የሚሆነው በውሰት ነው




ዩናይትዶች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የክርስቲያን ኤሪክሰንን ዝውውር ለማጠናቀቅ ብርቱ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ተአማኒው Sky sport ዘግቧል




ፈረንሳዊው የመድፈኞቹ የሗላ ደጀን ሎረንት ኮስሊኒ ከዘጠኝ አመት ቆይታ በኃላ የሀገሩን ክለብ ቦርዶን በ5ሚሊዮን ዩሮ ተቀላቅሏል
6ቁጥር መለያም እንደሚለብስ ታውቋል




ኤቨርተኖች የ2016 የአለም ዋንጫውን አሸናፊ ጅብሪል ሲዲቤን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል ሞናኮዎች ለጅብሪል ሲዲቤ እስከ £16m ይፈልጋል ኤቨርተንም ገንዘቡን ለመክፈል ፍቃደኛ ሆኗል




በርንማውዞች የሊቨርፑሉን ወጣት ተጨዋች ሀሪ ዊልሰንን በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርሟል



ማንችስተር ዩናይትድ ለክሪስ እስሞሊንግ ከኤቨርተን
የቀረበለትን የረጅም ጊዜ የዉሰት ዉል ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል ሀሪ ማጓየር ወደ ማንችስተር ማምራቱን ተከትሎ የቋሚነት ቦታዉን እንደሚያጣ የተገመተዉ እስሞሊንግም በማንችስተር ቆይቶ ለቦታዉ መታገልን መርጧል



ኖቲንግሀም ፎረስቶች የአርሰናሉን ካርል ጄንኪክሰንን አሥፈርመዋል ለዝውውሩ እስከ £2m ከፍለዋል በኖቲንግሀምም የሶስት አመት ውል አስፈርመውታል





የቀድሞው ማንቸስተር ዩናይትድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ዩራጋዊዩ አጥቂ ዲያጎ ፎርላን በ 40 አመቱ እራሡን ከእግር ኳስ አለም አግሏል




ማንችስተር ዩናይትዶች ከኤሪክሰን ዝውውር ጋር እያደረጉ የሚገኘውን ጥረት ማቋረጣቸውን BBC አስነብቧል ይሁን እንጂ ዩናይትዶች ቢያንስ ሁለት ተጫዋቾችን ለማዘዋወር ሙከራ እንደሚያደርግ ተሰምቷል




የዊልፍሬድ ዘሀ ዝውውር ሲከሽፍባቸው በድንገት ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አምርተው አሌክስ ኢዮቢን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል ኤቨርተኖች ለኢዮቢ £30m ያቀረበ ሲሆን አርሰናል ግን መነሻ £40m ብለው ዝውውሩን አቋርጠውታል




ክሪስታል ፓላስ የኤቨርተኑን ጀምስ ማካርቲን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ፓላስ ለማካርቲ እስከ £3m የሚያወጡ ይሆናል ከተጨዋቹም ጋ በግል ተስማምተዋል ዛሬ ወደ ለንደን በመብረር ሜዲካሉን እንደሚያደርግ ታውቋል



ያለፉትን አመታት በአርሰናል በጉዳት ጥሩ ጊዜ ያላሳለፈው እና በክረምቱ በነፃ ከአርሰናል የተለያየው ዳኒ ዊልቤክ ወደ ዋትፎርድ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሧል እስከነገም ዝውውሩ ተጠናቆ በይፋ የዋትፎርድ ተጨዋች ይሆናል




ዩናይትዶች ሙሉ በሙሉ ከክርስቲያን ኤሪክሰን ዝውውር እራሱን አውጥቷል ዩናይትዶች ኤሪክሰንን አናግረውት ወደ ስፔን ማምራት እንደሚፈልግ ስለነገራቸው ነው ዝውውሩን ያቋረጡት


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...