Tuesday, August 6, 2019

የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች



ባርሴሎና ኔይማርን ለማዘዋወር ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረገ እንዳልሆነ የባርሳው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆርዲ ካርዶኔር ተናግረዋል አሁን የማዘዋወር እቅድ ውስጥ አደለንም በፓሪስ ደስተኛ እንዳልሆነ እናውቃለን





በቅርብ ቀናት ሥሙ በሰፊው ከዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የነበረው ፓብሎ ዲባላ አሁን ደግሞ አዲስ ፈላጊ ክለብ ብቅ ብሏል የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ የልጁ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል ከፒኤስጂ ውጭ ኢንተርሚላንም ፈላጊው ነው




ለረጅም ጊዜ ከዩናይትድ ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዩናይትድ ምንም አይነት የዝውውር ጥያቄ እንዳላቀረቡ ታውቋል የስፖርቲንግ ሊዝበን ፕሬዝዳንትም እስካሁን ለብሩኖ ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው ተናግረዋል እስካሁን ድረስ ይፋዊ ጥያቄ ያቀረበው ማርሴ ብቻ ነው ተብሏል እሱም 32ሚዩ ነው ክለቡ ደግሞ 65ሚዩ ነው የሚፈልገው




እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ ኢንተር ሚላን ለሮሜሉ ሉካኩ £73m አቅርቧል ዩናይትድ ለልጁ እስከ £79m ይፈልጋሉ በቀናት ውስጥም ተደራድረው ሉካኩ ወደ ኢንተር መሄዱ አይቀርም ተብሏል




በአዲሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ እንደማይፈለግ የተነገረው ራጃ ናያንጎላን በብዙ ክለቦች ቢፈለግም በመጨረሻም በአንድ አመት የውሰት ውል ወደ ጣሊያኑ የቀድሞ ክለቡ ካግሊያሪ አምርቷል





ከማርሴይ ጋር ከተለያየ ቡሀላ እስካሁን ድረስ ክለብ ያላገኘው ማርዮ ባላቶሊ ወደ ብራዚል በማምራት ለፍላሚንጎ ለመጫወት እየተነጋገረ እንደሆነ ተነግሩዋል ከፍላሚንጎ በተጨማሪ ፊዮሬንቲና እና ቬሮና ይፈልጉታል ባላቶሊ ወደ ብራዚል የሚያመራ ከሆነ ከቀድሞ ጉዋደኛው ገብርኤል ባርቦሳ ጋር ሚጫወት ይሆናል





ፌሊፔ ኩቲንሆ ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ከስምምነት ላይ መድረሱን በርካታ ታማኝ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።በርካታ አርሰናል ላይ ትኩረት ያደረጉ ሚዲያዎችም በሰበር ዜናነት ዝውውሩ እንዳለቀ ዘግበዋል።አርሰናል ብራዚላዊውን ኮከብ በውሰት ለአንድ አመት ማዘዋወሩን ከሰዓታት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።



ሊዮኔል ሜሲ ጉዳት ደርሶበታል ከኮፓ አሜሪካ ውድድር ቡሀላ ትናንት ነበር የተመለሰው በመጀመሪያም የልምምድ ቀን የጡንቻ ጉዳት ደርሶበት ከልምምድ ወቷል እንዲሁም ባርሴሎና ወደ አሜሪካ አቅንቶ ከናፖሊ ጋር ከሚያደርገው የወዳጅነት ውጪ አድርጎታል እንዲሁም ባርሴሎና በስፔን ላሊጋ የመጀመሪያ ሳምንት ከአትሌቲኮ ቢልባኦ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ላይደርስ ይችላል ተብሏል ጉዳቱም እስከ ሶስት ሳምንት ከሜዳ እንደሚያርቀው ተሰምቷል




ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሩሲያ ያቀናው ብራዚላዊው ማልኮም ዜኒትን ሊለቅ ይችላል ተብሏል ምክንያቱም ማልኮም የመጀመሪያ ጨዋታውን ሲያደርግ የዜኒት ደጋፊዎች የዘረኝነት ባነር ይዘው ወተዋል ይህንንም ተከትሎ በዚ የዝውውር መስኮት ከተሳካ ሊሸጡት አልያም ካልተሣካ በጥር የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ፍላጎት አላቸው




በቸልሲ ሰባት አመታትን ያሳለፈው የ33አመቱ እንግሊዛዊው ተከላካይ ጋሪ ካሄል ክርስቲያል ፓላስን ተቀላቅሏል ፓላስ ካሂልን በሁለት አመት በነፃ የዝውውር ሂሳብ አስፈርሞታል በፓላስም እስከ 35አመቱ ድረስ ይቆያል




ቶተንሀም £30m እና ጆሽ ኦናምን ለፉልሀም ለመስጠት ሪያን ሴሴኞንን ማስፈረም ይፈልጋሉ ዝውውሩም የመጠናቀቅ እድል እንዳለውም መረጃዎች እያሳዩ ይገኛል




ማውሮ ኢካርዲ እና ኢንተር ሚላን ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ተሰምቷል ኢንተሮች ተጨዋቹን መሸጥ ይፈልጋል ነገር ግን ተጨዋቹ እና ወኪኩ ዋንዳናራ ለዝውውር የሚመጡ ጥያቄዎችን ውድቅ አድርገዋል ክለቡ ለቀጣይ ሁለት አመታት ክለቡን ማይለቅ ከሆነ ተጠባባቂ ወንበር ላይ እንደሚያስቀምጡት ተሰምቷል





በቶተንሀም የ12ወራት ኮንትራት የሚቀረው ቤልጄማዊው ያን ቬርቶጋን ስለ ቆይታው ተጠይቆ ምላሽ ሰቷል ስለ ወደፊቴ ምንም አላቅም በቶተንሀም ደስተኛ ነኝ ጥሩ የውድድር ጊዜ እያሳለፍኩ ነው በቀጣይ ግን በቶተንሀም ልቆይ አልቆይ ማቀው ነገር የለም ብሏል




ቶትንሃም ሆትስፐሮች ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ወኪል ጋር በተጫዋቹ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ፖርቱጋላዊው ጋዜጠኛ Gonçalo Lopes.ዘግቧል ነገር ግን ሁለቱ ክለቦች ከስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም ቶትንሃሞች ለተጫዋቹ ዝውውር 50ሚዩ ተጨማሪ 10ሚዩ የተጫዋቹ አቋም እየታየ የሚጨመር ሂሳብ ነው ማቅረብ የሚፈልጉት ባንፃሩ ስፖርቲንግ ሊዝበኖች ከተጫዋቹ ሽያጭ 70ዩሮየዝውውር ሂሳብ ነው የሚፈልጉት




ዋይኒ ሩኒ በይፋ ለሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ለደርቢ ካውንቲ ፈርሟል የሚመጣው ጃንዋሪ ወር ላይ ሩኒ አሁን ካለበት ከዲሲ ዩናይትድ ወጥቶ ወደ ደርቢ ካውንቲ በመሄድ በተጫዋቾች አሰልጣኝነት እንደሚያገለግል ታውቋል




ሊዮሬ ሳኔ በ110ሚዩ ወደ ባየርን ሙኒክ ሊያመራ ተቃርቧል 18ሚዩ በአመት ይከፈለዋል የቡንደስሊጋውም ውዱ ተከፋይ እንደሚሆን ተነግሯል




ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ቶተንሀሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን አዙሯል ዩናይትዶች የአምስት አመት ኮንትራት እና ከፖግባ እኩል 290.000 ሳምንታዊ ደሞዝ ማቅረቡ ተሰምቷል ልጁም ቶተንሀምን መልቀቅ ይፈልጋል ልጁ £60m ቶተንሀሞች ይፈልጋሉ ግን ዳኒ ሌቪ ለአንግሊዝ ክለቦች £130m  በታች እንደማይሸጠት ተናግረዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...