Monday, August 5, 2019

የሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ከትናንቱ የካምፕኑ ምሽት ጨዋታ በፊት የአርሰናል እና የባርሳ ሰዎች በኩቲንሆ ዝውውር ጉዳይ ንግግር ማድረጋቸው ተሰምቷል አርሰናል ለአንድ አመት የውሰት ውል £27m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆኗል በቀጣይ አመትም ቋሚ ማድረግ እንደሚፈልጉ ነግረዋቸዋል




በክረምቱ ከቸልሲ የተለያየው ጋሪ ካሄለ ወደ ክርስቲያል ፓላስ የማምራት ሰፊ እድል እንዳለው ተሰምቷል የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን እንዳሳመኑት እና በለንደን መቆየትም ስለሚፈልግ ወደ ፓላስ ማምራቱ የማይቀር ይመስላል




በብዙ ክለቦች የሚፈለገውን ቫንድቢክን ሪያል ማድሪድ ለማስፈረም ተቃርቧል የሚል መረጃ ወቷል በአያክስ ፍላጎት እና ሪያል ማድሪድ ለመስጠት በፈለገው ዋጋ ያለው ልዩነት £5m ነው በዚም ተስማምተው ዝውውሩ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል




ኢንተር ሚላኖች የተሻሻለ ሂሳብ ለሮሜሉ ሉካኩ አቅርበዋል አቀረቡት የተባለው ሂሳብ እስከ £70m ተብሏል ዩናይትዶችም የኢንተሮችን ጥያቄ እንደሚቀበሉ ይጠበቃል ሉካኩ እዛው ጣሊያን ከኢንተር በተጨማሪ በጁቬንቱስ እና በናፖሊ ይፈለጋል




አሰልቺው የሀሪ ማጉዋየር ዝውውር ዛሬ ተጠናቋል ዩናይትድ በይፋ አስፈርሞታል በአለም የተከላካዮች ሪከርድ በሆነ ዋጋ ኦልትራፎርድ የደረሰው ማጉዋየር በዩናይትድ 6አመት ለመቆየት ውል ፈርሟል ሪዮ ፈርዲናንድ ይለብሰው የነበረውን 5 ቁጥር እንደሚለብስም ታውቋል




ሪያል ማድሪድ ለፖል ፖግባ ያቀረቡት የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ተደርጎባቸዋል ማድሪድ ለፖግባ £27.6m እና ሀሜስ ሮድሪጌዝን ቢያቀርብም ዩናይትዶች ውድቅ አድርገዋል




ሲሞን ሚኞሌትን ወደ ክለብ ብሩጅ የሸኙት ሊቨርፑሎች አዲስ ግብ ጠባቂ አሥፈርመዋል የቀድሞ የዌስትሀሙን ግብ ጠባቂ አድሪያንን የአሊሰን ቤከር ተጠባባቂ ለማድረግ በነፃ የዝውውር ሂሳብ አስፈርመውታል




ሮማ በተለያዩ የጣሊያን ክለቦች የሚፈለገውን እንዲሁም በኢንተር ሚላን የዝውውር ጥያቄ የቀረበለትን ኤዲን ዤኮን ለሚፈልግ ማንኛውም ክለብ እስከ £20m እንደሚፈልጉ እና ይሄን ገንዘብ ለሚያቀርብ ክለብ እንደሚሸጡት ይፋ አድርገዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...