Monday, August 5, 2019
የሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
ከትናንቱ የኮሚኒቲ ሺልድ ድል በኃላ ፔፕ ጋርድዮላ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሀሪ ማጉየርን እንፈልገው ነበር ነገር ግን ዩናይትድ አግኝቶታል ለዚያም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ፈልጋለሁ እሱ ምርጥ እና world class ተጫዋች ነው በአለም ዋንጫው ብሄራዊ ቡድን አቅሙን አሳይቷል
እሱ ከካስ ጋር አሪፍ ነው እሱ በአየር ካስ አሪፍ ነው ፈጣን እና ምርጥ የቡድን ተጫዋቸ ነው
ለዚህ ፊርማም የዩናይትድን እንኳን ደስ አላቹ ብሏል ፔፕ ጋርዲዮላ
አሰልቺው የፓብሎ ዲባላ ዝውውር ወደ መቋጫው ተቃርቧል ዲባላ የጠየቀውን 350.000 ሳምንታዊ ደሞዝ ጠይቋል ዩናይትዶች ደግሞ ይሄንን የመክፈል ፍላጎት የላቸውም ትናንት ከብዙ ጊዜ ድርድር ቡሀላ በይፋ ዝውውሩን አቋርጠውታል
ኢንተር ሚላን በድጋሚ የሮሜሉ ሉካኩ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል በዚ ሳምንት በስፋት ከጁቬ ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል አሁን ላይ ወደ ጁቬ መሄዱ ሚሳካ አይመስልም እና ኢንተር በፊት ካቀረበው £53.3m የተሻሻለ ገንዘብ ይዞ እንደሚቀርብ ተሰምቷል ኮንቴም ልጁን እንደሚፈልጉትም ትናንት ተናግረዋል
ዩናይትዶች ማርዮ ማንዙኪችን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል በጁቬ ቋሚ ቦታ እንደማያገኝ ያወቀው ማንዙኪች ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል ዩናይትድ በአመት £6.2m የሚከፍለው ሲሆን በዩናይትድ 2022 የሚቆይ ይሆናል
በእሁዱ የኮሚኒቲሺልድ ጨዋታ ተጠባባቂ ወንበር ላይ የነበረው የሊቨርፑሉ ሲሞን ሚኞሌት ወደ ክለብ ብሩጅ ለማምራት ከስምምነት ላይ ደርሷል ዛሬ የህክምና ምርመራውን የሚያደርግ ሲሆን ክለብ ብሩጅ ለሊቨርፑል £6m እንደሚከፍሉ ታውቋል
ማንችስተር ሲቲ የጁቬንቱሱን ጃኦ ካንሴሎን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ሲቲ ለካንሴሎ £27M እና ዳኒሎን በመስጠት ከስምምነት ደርሰዋል በሰአታት ውስጥም ዝውውሩ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል
ቶተንሀም ጆቫኒ ሌሴልሲዮን ከሪያል ቤትስ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ቶተንሀም ለዝውውሩ £52m እና ታይቶ የሚጨመር £8m ይከፍላል ቶተንሀም ለልጁ በአመት £4M የሚከፍል ሲሆን በቶተንሀም ለአምስት አመት የሚያቆየውን ውል ይፈርማል
ብራይተን ሆብ አልቢዮን በቸልሲ የማይፈለገውን እንግሊዛዊ አማካይ ዳኒ ድሪንክ ወተርን በአንድ አመት የውሰት ውል ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ እና የአሁን የክርስቲያል ፓላስ ኮከብ ዊልፍሪድ ዛሀ ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር በኒኮላስ ፔፔ ዝውውር ምክንያት መቅረቱ አይረሴ ነው አሁን ደግሞ ዛሀ የብሄራዊ ቡድን አጋሩን የኤሪክ ቤሊን 3 ቂጥር መለያ በመልበስ ልምምድ እያደረገ ታይቷል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment