Sunday, August 4, 2019

የእሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ማንቸስተር ሲቲዎች በ 30 ሚሊየን ፓውንድ እና ዳኒሎን ለ ጁቬንቱስ በመስጠት ጃኦ ካንሴሎን ከጁቬንቱስ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል




ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት ወደ ዩናይትድ መመለስ እንደሚፈልግ ተዘገበ እንደ ዘ ሰን ዘገባ ከሆነ የ33 አመቱ እንግሊዛዊ ተጫዋች ረጅም ጊዜ በተጫዋችነት ያሳለፈበትን ቤት ኳስ ሲያቆም በአሰልጣኝነት ማገልገል ይፈለጋል




ሮማዎች የዜኮን የመሸጫ ዋጋ በ20 ሚ.ዩሮ አሳድገውታል ኢንተር የተጫዋቹ ፈላጊ ሲሆን 17 ሚ.ዩሮ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ሮማዎች ተጨማሪ 20 ሚ.ዩሮ ጠይቀዋል




ጁቬዎች ካንሴሎን ለማንሲቲ የሚሸጡ ከሆነ በምትኩ ሁዋን ሚራንዳን  ለማስፈረም አስበዋል




ኢንተሮች መሀላቸውን ለማጠናከር ራኪቲችን ከባርሴሎና ወይም ስትሩትማንን ከማርሴይ ለማስፈረም ይፈልጋሉ




ኤሲ ሚላን እስማኤል ቤናሰርን ከኢምፖሊ አስፈረመ የ21 አመቱ አማካኝ በአፍሪካ ዋንጫው ከአልጀሪያ ጋር ምርጥ አቋሙን በማሳየት ሻምፒዮን የሆነ ሲሆን በኢምፖሊ የሁለት አመት ቆይታ አድርጓል




ማንችስተር ሲቲዎች ዘግይተውም ቢሆን ለሪያል ማድሪዱ ኢስኮና ለበርንማውዙ ናታን አኬ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው




የአያክሱ አማካይ ዶኒ ቫን ደቢክ ሪያል ማድሪዶች እንደሚፈልጉትና ከክለቡ ጋር ንግግር  ላይ እንደሆኑ ተናገረ ፖል ፖግባን ማምጣት ያልቻሉት ማድሪዶች 55 ሚ.ፓ የተገመተውን ተጫዋች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ያስፈርሙታል ተብሎ ይጠበቃል




ባርሴሎናዎች የ ሪያል ቤቲሱን የግራ መስመር ተከላካይ ጁኒየር ፊርፖን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል




ኤቨርተን የሞይስ ኪንን ዝውውር ይፋ አድርጓል ጣሊያናዊው ወጣት በጉዲሰን ፓርክ እስከ 2024 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...