Sunday, August 4, 2019

የእሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች




አርሰናል ፊሊፕ ኩቲንሆን ከባርሳ በውሰት ለማምጣት ፍላጎት አሳይተዋል አርሰናሎች ከባርሳ ጋር ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ናቸው አርሰናሎች ከተሳካላቸው በሁለት አመት የውሰት ውል ያስፈርሙታል ተብሏል




አምና በኤሲሚላን በውሰት ያሳለፈው ባካዮኩ እና በማውሪዚዮ ሳሪ ስር አመቱን በተጠባባቂ ያሳለፈው ድሪንክ ወተርን ቸልሲዎች ሊለቁዋቸው እንደሚፈልጉ ተሰምቷል




ፓውሎ ዲባላን በሮሜሉ ሉካኩ የመቀየር ውል ለጊዜው ቆሟል  ምክንያቱ ደግሞ ዲባላ ጋር እስካሁን በግል ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ከማንቸስተር ዩናይትዶች ጋር ባለመስማማቱ ነው




ወልቨርሀምፕተን ዋንደረርስ ፖርቹጋላዊዎቹን ወጣት ተጫዋቾችፔድሮ ኔቶን እና ብሩኖ ጃርዳኦን በረዥም አመት ውል ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል




ዋትፎርዶች ለ አብዱላይ ዶውኮሬ ኤቨርተኖች ያቀረቡትን የ 32 ሚሊየን ፓውንድ ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል የሜርሴሳይዱ ክለብ ያቀረቡትን ገንዘብ ጨምረው ሁለተኛ ዙር ውል እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል




ከቀናት በፊት ዳኒ አልቬስን በነፃ የዝውውር ሂሳብ ያስፈረሙት ሳኦ ፓውሎዎች አሁን ደግሞ ከኮንትራት ነፃ የሆነውን የቀድሞ የአትሌቲኮ ማድሪድ ተጨዋች ሁዋን ፍራንን በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውታል




ኤሲሚሌን  የዩዲኔዜውን ኮከብ ሮድሪጎ ዲፖልን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው እንደ ቱቶ መርካቶ ዘገባ ለተጨዋቹ እስከ 40ሚዩ እንደሚያሶጣቸው ተነግሯል




ሀሪ ማጉየር በመጨረሻም ዛሬ ወደ ጋሪንግተን ለሜዲካል ሲያመራ ታይቷል ዝውውሩም ነገ ይፋ ይሆናል ከአንድ አመት በላይ በጥብቅ ሲፈልጉት ለነበሩት ዩናይትዶች በመጨረሻም እፎይታን ሰቷቸዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...