Saturday, August 3, 2019

የቅዳሜ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


ሪያል ማድሪዶች ስሙ የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ ጀምሮ ከዩናይትድ ጋር እንዲሁም ከቅርብ ሳምንታት ጀምሮ ደግሞ ከቶትንሃሞች ዝውውር ጋር በሰፊው እየተያያዘ የሚገኘው ፖርቱጋላዊውን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማዘዋወር የሚደረገውን ትንቅንቅ ተቀላቅሏል በተጨማሪም ሪያል ማድሪዶች ከተጫዋቹ ወኪል ጆርጊ ሜንዴዝ ጋር ድርድር ላይ መሆናለውን ከወደ ፓርቱጋል እየወጡ ያሉ መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ




 ዩናይትዶች የቶትንሀሙን የመሀል ሜዳ ኮከብ ክርስቲያን ኤርክሰንን ለማዘዋወር የነበራቸው ፍላጎት እንደ አዲስ አገርሽቶባቸዋል ሲል independent አስነብቧል ኤሪክሰን በቶትንሃም ቤት የ12ወራት ኮንትራት ብቻ ነው የቀረው ሊያጡት እንደሚችሉ ያሰቡት ስፐርሶች የኤሪክሰን ምትክ ይሆንላቸው ዘንድ ጆቫኒ ሎሴሎን ከሪያል ቤቲስ አልያም ብሩኖ ፈርናንዴዝን ከስፖርቲንግ ሊዝበን ለማዘዋወር ጥረት ጀምረዋል




ቫንሀል ፔፕ ጋርዲዮላ በሙኒክ እና በሲቲ በአውሮፓ ስኬታማ አለመሆኑ ሊያስተቸው ይገባል ብሏል እርግጥ ነው በፕሪሚየር ሊጉ በተከታታይ ማሸነፉ አስደናቂ ነው ግን የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ አለመሆኑ ሊያስተቸው ይገባል ብለዋል




ቤልጄማዊው የቶተንሀም ተከላካይ ቶቢ አልደርዊልድ ወደ ሮማ መሄድ እንደሚፈልግ ተሰምቷል ቶተንሀም ለተጨዋቹ 28ሚዩ ይፈልጋል ሮማ 28ሚዩ መክፈል አንችልም 20ሚዩ እንደሚከፍሉ ታውቋል




ክርስቲያል ፓላስ የሪያል ቤትሱን  አማካይ ቪክተር ካማራስን ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው ከ12-15ሚዩ ለሪያል ቤትስ ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል




ማንችስተር ዩናይትዶች ለአያክሱ ብራዚላዊ ኮከብ ዴቪድ ኔሬስ 50ማሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ቢያቀርቡም አያክሶች ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል ከተጫዋቹ ሽያጭ ቢያንስ 70ሚሊዮን ዩሮ ነው አያክሶች የሚፈልጉት




አትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሀም ሆትስፐር በቦሩሲያ ሞንቼግላድባው ማቲያስ ጊንት ላይ ፍላጎት አሳይተዋል ሁለቱም ክለቦች ለተጨዋቹ እስከ £35m መክፈል ይፈልጋሉ ሞንቼግላድባ ለልጁ እስከ £60m ይፈልጋል




ኤቨርተን ጂያን ፒሊፔን ከጀርመኑ ሜንዝ 05  አስፈርሟል ኤቨርተን ለተጨዋቹ £27m ይከፍላሉ በኤቨርተንም የአምስት አመት ውል የፈረመ ሲሆን በክለቡም 25 ቁጥር መለያን ይለብሳል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...