Saturday, August 3, 2019

የቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች


ዩናይትዶች ሁለት ዝውውሮችን ለመጨረስ ተቃርበዋል የሌስተሩ ሀሪ ማጉዌር መግባቱ የተረጋገጠ ሲሆን ሌላኛው ፈራሚ ደግሙ ፈርናንዴዝ ነው ክለቡ ስፖርቲንግ ሊዝበን ነገ ከቤኔፊካ ጋር ከሚያደርገው የፖርቱጋል ሱፐር ካፕ ፍፃሜ ቡሀላ የዩናይትድ ንብረት መሆኑ እርግጥ ይሆናል




ማንችስተር ሲቲዎች ጃኦ ካንሴሎን ለማስፈረም ከመቼውም በላይ ፍላጎት አሳይተዋል እንደውም ከቀናት በፊት በለንደን ከጁቬንቱስ ሰዎች ጋር በይፋ መነጋገራቸው ተሰምቷል ሲቲዎች ለጁቬ ገንዘብ እና ዳኒሎን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ታውቋል




ናፖሊ ኒኮላስ ፔፔን በአርሰናል መነጠቃቸውን ተከትሎ ፊታቸውን ወደ ፒኤስቪው ሜክሲኮያዊው አጥቂ ሂርቢን ሎዛኖን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው ጥሩ ጉዞ ላይም እንዳሉ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል





ዳርዮ ቤኔዲቶ ወደ ማርሴ ሚያደርገውን ዝውውር ሊያጠናቅቅ እንደተቃረበ የቦካ ጁኒየርሱ ፕሬዝዳንት አረጋግጠዋል  ማርሴ ለቦካ £15m ሚከፍል ይሆናል በማርሴም 4አመት ኮንትራት ሚፈርም ሲሆን ዛሬ የህክምና ምርመራ ያደርጋል




የማንችስተር ዩናይትዱ ሌጀንድ ክርስቲያኖ ሮናልዶ
ከፓብሎ ዲባላ ጋር በዋትስአፓ ንግግር አደርገው እንደነበር ተሰምቷል ሮናልዶ ዲባላን ዩናይትድን ቢቀላቀል ባለድል እንደሚሆን መክሮታል



ከባየርን ሙኒክ ከለቀቀ ቡሀላ ወደ ጣሊያን አልያም እዛው ጀርመን ውስጥ ይቆያል የተባለው ፈረንሳዊው ኮከብ ፍራንክ ሪቤሪ በመጨረሻም ወደ እስያ ሊያመራ እንደሆነ ተሰምቷል እንደ መረጃው ከሆነ ሪቤሪ ወደ ኳታር አልያም ወደ ሳኡዲ አረቢያ ያመራል




ሀሪ ማጉዋየርን በአለም የተከላካዮች ሪከርድ በሆነ ዋጋ ለዩናይትድ የሸጡት ሌስተሮች በሱ ቦታ ተከላካይ ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ከዚህ በፊት ስሙ ከሌስተር ጋር የተነሳው የብራይተን ተከላካይ ልዊስ ደንክ ዋነኛ ኢላማቸው ነው ብራይተኖች ከተከላካዩ እስከ £40m ይፈልጋሉ




ኤቨርተን ወጣቱን ጣሊያናዊ አጥቂ ለማስፈረም ተቃርቧል እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ዛሬ በሊቨርፑል ከተማ ተገኝቶ የህክምና ምርመራውን ያደርጋል ኤቨርተን ለተጨዋቹ £40m ይከፍላል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...