Friday, August 2, 2019
የአርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አርሰናል ለሳሚ ከዲራ 4ሚዩ ለመክፈል ፍቃደኛ ሆኗል በጁቬንቱስ 6ሚዩ ነው ሚከፈለው በዘንድሮ የጁቬንቱስ ስብስብ ውስጥ ቦታ እንደሌለው የተነገረው ከዲራን ለማስፈረም ብዙ ክለቦች ይፈልጋሉ
ማንችስተር ዩናይትዶች ለመጨረሻ ጊዜ ለሀሪ ማጉዋየር ዝውውር ያቀረቡት £80m በሌስተሮች ተቀባይነት አግኝቷል በሚል sky sport አስነብቧል ይህንን ተከትሎ የማጉየር ዝውውር ከተቋጨ የአለም የተከላካዮችን የዝውውር ክብረ ወሰን የሚጨብጥ ይሆናል
እንደ ጋዜጣ ዴሎስፖርት ዘገባ ከሆነ አርሰናል ዳንኤል ሩጋኒን ከጁቬንቱስ በሁለት አመት የውሰት ውል ማስፈረም ይፈልጋል ጁቬንቱስ በዚ የውድድር አመት ልጁን የመጠቀም ፍላጎት ባይኖራቸውም በቀጣይ አመታት ልጁን ሊጠቀሙበት ስለሚፈልጉ ልጁን መሸጥ አይፈልጉም ነገር ግን ልጁን በውሰት በመስጠት በቀጣይ አመታት መልሰው ማጫወት ይፈልጋሉ
ሮማዎች ከኤዲን ዤኮ ዝውውር £20M ይፈልጋሉ ኢንተሮች ደግሞ ለዤኮ ከ£15M ነው መክፈል ሚፈልጉት የዤኮ ወደ ኢንተር ሚያደርገው ዝውውር ኢካርዲን እንዲወጣ ያደርገዋል ይህንንም ተከትሎ ኢካርዲ ሮማን እንደመረጠ ተሰምቷል ዝውውሩም የመሳካት እድሉ ሰፊ ነው
ክሪስታል ፓላስ በዊልፍሬድ ዘሀ ዝውውር ላይ ናፖሊ መግባቱን ተከትሎ ዋጋውን ከፍ ሊያረጉት አስበዋል ፔፔን በአርሰናል የተነጠቁት ናፖሊዎች ለዘሀ £60m እንዳቀረቡ ተሰምቷል ከቀናት በፊት ኤቨርተኖች ልጁን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል መባሉ ይታወሳል አሁን ላይ የሁለቱ ክለቦች ፍላጎት በማጤን የዝውውር ሂሳቡን ከ£80m በላይ ለማረግ እንደፈለጉ ተሰምቷል
እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ቶተንሀም ሎሴልሲዮን ለማስፈረም ተቃርቧል የሚል መረጃ ይዞ ወቷል ፈኪርን ያስፈረሙት ሪያል ቤትሶች ሎሴልሲዮን ለመልቀቅ ይፈልጋሉ አርጀንቲናዊው አማካይ ወደ ቶተንሀም ማምራት ይፈልጋል ቶተንሀም በአመት 4ሚዩ ይከፍሉታል ለቤትሶች 60ሚዩ ይከፍላሉ
ኡናይ ኤምሪ ሎረንት ኮሸሌኒን በክለቡ ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል እስካሁንም ድረስ የመሀል ተከላካይ ያላስፈረሙት ይህ ተጨዋች በክለቡ ይቆያል በሚል ሀሳብ ነው ወደ ስታደሬን ሚያመራ ከሆነ ግን አንድ ተጨዋች እንደሚያስፈርሙ ተነግሯል
ሪያል ማድሪድ ፊቱን ወደ አያክሱ አማካይ ቫን ዲቤክ እንዳዞረ ተሰምቷል የፖል ፖግባ በዩናይትድ መቆየትን ተከትሎ ማድሪዶች ሌላ አማካይ ፍለጋ ወተዋል ባሳለፍነው ሳምንት የአያክሱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለባቸው ተጨዋች ሻጭ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል ይህንን ተከትሎ ማድሪድ ልጁን የማግኘት ትልቅ እድል ተፈጥሮለታልም በቅርብ ጊዜም ዝውውሩ የመሳካት እድል እንዳለው ተሰምቷል
ማውሪዝዮ ሳሪ በሁለት ተጨዋቾች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል ተብሏል እነሱም ዳግላስ ኮስታ በክለቡ እንዲቆይ ማሪዮ ማንዙኪች ደግም ክለቡን እንዲለቅ እንደሚፈልጉ ውሳኔ አሳልፈዋል የኮስታ ቆይታ የተወሰንው ከማንዙኪች የተሻለ ግልጋሎት ስለሚሰጥ ነው
የኖንቱ አሰልጣኝ ቫሂድ ሀሊድ ሆዚች ከዛሬ ምሽቱ የጄንዋ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ጨዋታ በሗላ ክለቡን እንደሚለቁ ታውቋል ባለፈው የውድድር አመት አጋማሽ ነበር ኖንትን የተረከቡት ከሊጉም እንዳይወርድ ታድገውታል ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር በዝውውር እቅድ ዙሪያ መግባባት አልቻሉም ለዛም ነው ሚለያዩት ተብሏል
በብዙ ክለቦች የሚፈለገው ብራዚላዊው ማልኮም ማረፊያው ሩሲያ ሊሆን ተቃርቧል ሴኔትስበርጎች ለባርሴሎና 45ሚዩ ከፍለዋል ኤቨርተን በመጨረሻ ሰአት ልጁን ከዜኒት ለመጥለፍ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም በመጨረሻም ማረፊያው ሩሲያ ሆኗል
የአርሰናሉ ተከላካይ ክርስታን ቤሊክ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ደርቢ ካውንቲ ተቃርቧል ደርቢ £10m ለአርሰናል ይከፍላል 2015 ነበር ከሊጋ ዋርሶ ያስፈርመው በተለያየ ጊዜ በውሰት ያሳለፈው ቤሊ በመጨረሻም ማረፊያው ለማምራትደርቢ ለማምራት ተቃርቧል ዝውውሩም ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል
ኢንተር ሚላን ባለቀ ሰአት ዲባላን ከጁቬንቱስ ለመውሰድ አስበዋል ሉካኩን በዲባላ ለመቀየር እየተዘጋጁ ለነበሩት ዩናይትዶች መጥፎ ሚባል ዜና ሆኗል ኢንተሮች ድርድር እንደጀመሩም ተሰምቷል ኢካርዲም የዝውውሩ አካል በመሆን ወደ ቱሪን ሊያመራ እንደሚችል ተሰምቷል
ማንችስተር ዩናይትድ እና ሌስተር በማጉዌር ጉዳይ በመጨረሻ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የተለያዩ የእንግሊዝ ሚድያዎች ከደቂቃ በፊት በሰበር መልክ እንዳስነበቡት ዩናይትድ የአለም የተከላካይ ሪከርድ በሆነ ዋጋ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል እንደ MEN ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ ነገ በካሪንግተን የህክምና ምርመራውን ያደርጋል
በመጨረሻም ሼፍልድ ዩናይትድ የክለቡን ሪከርድ በመስበር ኦሊ ማክብሩኒን ከስዋንሲ ሲቲ በ£20m አስፈርሞታል በሼፍልድም አራት አመታትን የሚያቆየውን ውል ፈርሟል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment