Thursday, August 1, 2019

የሀሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች



ጀርመንኛ እየተማሩ የሚገኙት ጆዜ ወደ ጀርመን ይሄዳሉ ተብሎ ብዙ ሲወራ ነበር ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቫሌንሲያ ሊያመሩ እንደሚችሉ ተሰምቷል ቫሌንሲያ ከሰሞኑ ከማርሴሊኖ ጋር የሚለያይ ከሆነ  ጆዜን ወደ ክለቡ ለማምጣት ይፈልጋሉ




ሼፍልድ ዩናይትድ አራተኛ የክለቡን የዝውውር ሪከርድ ለመስበር ተቃርቧል £20m ከፍሎ የስዋንሲውን አጥቂ ኦሊማክ ባርኒን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል




ጁኒየር ፊርፖ ከሪያል ቤትስ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ተስማምቷል በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ በጥብቅ ሲፈለግ ነበር ባርሳ በመጀመሪያ የዝውውር ጥያቄው 18ሚዩ እና እየታየ የሚጨመር 5ሚዩ አቅርቦ ነበር ቤትሶች ደግሞ 20ሚዩ እና ብቃቱ እየታየ 7ሚዩ እየታየ የሚጨመር ነው የሚፈልጉት በመጨረሻም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል




ማንችስተር ሲቲ ሚካኤል ኦያርዞባን ከሪያል ሶሴዳድ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረው እንደነበር ይታወቃል አሁን ላይ ግን ፍላጎቱን አንዳነሳ ታውቋል 75ሚዩ ውል ማፍረሻው ነው ይሄንን ደግሞ ሲቲ መክፈል አይፈልግም ሪያል ሶሴዳድ ደግሞ ውል ማፍረሻው ካልተከፈለው በምንም አይነት መልኩ ልጁን መሸጥ አይፈልጉም




በሊቨርፑል በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው የበርንሌው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በመጨረሻም ወደ አስቶንቪላ ለማምራት ተቃርቧል አስቶንቪላ ለበርንሌ £8m ለመክፈል ተስማምቷል




 ሞናኮ አጥቂውን ራዳሜል ፋልካኦን ለጋላታሳራይ ለመሸጥ ድርድር ላይ መሆናቸው ተስምቷል ፋልካኦ በሞናኮ ተጨማሪ አንድ አመት ኮንትራት ቢኖረውም ወደ ቱርክ ለማምራት ተቃርቧል




ኤቨርተን ሄነሪ ኦኔኩን ለማስፈረም ከሞናኮ ጋር ንግግር ጀምረዋል ነገር ግን የዚህ ተጨዋች ዝውውር ትልቅ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ ሚነገረው በእንግሊዝ የስራ ፍቃድ አለመኖሩ ነው




ቶተንሃሞች አርጀንቲናዊውን የሪያል ቤቲስ የአጥቂ አማካይ ጆቫኒ ሎሴሎን ዝውውር በ€60ሚዩ ለመጨረስ ተቃርበዋል ሪያል ቤቲሶች የሎሴሎ ምትክ ይሆናቸው ዘንድ ናቢል ፈኪርን ማስፈረማቸው አይዘነጋም




በአዲሱ የኢንተር ሚላን አሰልጣኝ ኮንቴ አትፈለግም የተባለውን ማውሮ ኢካርዲ አዲስ ክለብ ለማግኘት ተቃርቧል ከኢንተር ጋር ስሙ እየተነሳ የሚገኘው ኤዲን ዤኮ ዝውውር ሚሳካ ከሆነ በተቃራኒው ኢካርዲ ወደ ሮማ ማምራት የሚችልበት አጋጣሚ ተፈጥሮለታል




አንድሬ ሹርለ ወደ ሩሲያው ስፓርታክ ሞስኮ መዘዋወሩን ቦሩሲያ ዶርትመንድ ይፋ አድርጓል ሹርለ ባሳለፍነው አመት በፉልሀም በውሰት እንደቆየ ይታወሳል አሁንም ወደ ስፓርታ ሞስኮ በውሰት አምርቷል



ፊሊፔ ኩቲንሆ በባርሳ ብዙም እየተፈለገ አደለም ሙንዶ ዲፖርቲቮ የተባለው የባርሴሎና ጋዜጣ እንዳስነበበው ባርሴሎና ተጨዋቹን መሸጥ ይፈልጋል ግን እስካሁን ድረስ ይሄንን ተጨዋች ለመግዛት ሂሳብ ይዞ የመጣ ስለሌለ በቀጣይ አመት በካምፕኑ ይቆያል




እንደ ሌኪፕ ዘገባ ከሆነ ሄንድሪ ኩሩ ወደ ሞናኮ ሊዘዋወር እንደሆነ ለጉዋደኞቹ ነግሮዋቸዋል ንብረትነቱ የኤቨርተን ነው ባሳለፍነው የውድድር አመት በጋላታሳራይ በውሰት አሳልፏል ኤቨርተኖች እስካሁን ተጨዋቹን አልተጠቀሙበትም አሁን ሞናኮ 15ሚዩ በመክፈል ሊያስፈርሙት ተቃርበዋል




እንደ ስፖርት የተባለው ዘገባ ከሆነ ፒኤስጂ ለኔይማር እስካሁን እነሱ ሚፈልጉትን ሂሳብ ሊያቀርብ የሚቸል ክለብ ስላላገኙ ለአንድ አመት ኔይማርን እንዲቆይ እየጠየቁት ነው አዲስ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊዮናርዶ አሁን ፒኤስጂ ወደ ሚገኝበት ቻይና በማምራት መነጋገር ይፈልጋል ተብሏል




ትናንት ማምሻውን ሁለት የጣሊያን ጋዜጦች ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ ጁቬንቱስ በሉካኩ ዝውውር ላይ ከዲባላ በተጨማሪ ማርዮ ማንዙኪችን ሰተው ሉካኩ ወደ ጁቬንቱስ እንዲመጣ ፍላጎት አሳይተዋል




የጣሊያናዊው አጥቂ ሞይስ ኪን ዝውውር ዛሬ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተነግሯል የተጨዋቹ ወኪል ሚኖ ራዮላ ወደ ሊቨርፑል ከተማ ደርሷል አሁን ሚቀረው የጥቅማ ጥቅም ጉዳይ ብቻ ነው እሱ እንደተጠናቀቀ ሞይስ ኪን አዲሱ የኤቨርተን ተጨዋች ይሆናል




በእንግሊዝ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው የክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ አሁን ደግሞ ከወደ ጣልያን ክለብ ፈላጊ አግኝቷል የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ ለማስፈረም £60m ለክሪስታል ፓላስ አቅርቧል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...