Wednesday, July 31, 2019

የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


አርሰናል በብዙ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን እና ብዙ ጊዜ ከክለቡ ጋር ይነሳ የነበረው የ22አመቱን የሴልቲክ የግራ መስመር ተከላካይ ኬራን ቴርኒን ለማስፈረም ከስምምነት እንደደረሰ ታማኝ የሚባሉ የመረጃ ምንጮች ዛሬ ጠዋት አስነብበዋል




ብራዚላዊው የክንፍ ተጫዋች ማልኮም ወደ ዜኒት ፒተርስበርግ የሚያደርገው ዝውውር በ€40ሚሊዮን ዩሮ ለመጠናቀቅ ተቃርቧል በተጨማሪም የተጫዋቹ አቋም እየታየ ዜኒቶች ለብሉግራናዎቹ €5ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ክፍያ የሚጨምሩ ይሆናል




አርሰናል የጁቬንቱሱን አጥቂ ሞይስ ኪንን ዝውውር ከኤቨርተን ለመጥለፍ ሙከራ ቢያደርጉም ተጫዋቹ ወደ ጉዲሰን ፓርክ ነው መቀላቀል የሚፈልገው ምክንያቱም በቂ የመሰለፍ እድል ማግኘት ስለሚፈልግ ነው




ከጊዜ ወደ ጊዜ የሀሪ ማጉየር ሂሳብ እየተጨመረባቸው የሚገኙት ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ሳሙኤል ኡምቲቲ ሊያዞሩ መሆኑን እንዲሁም €50ሚሊዮን ዩሮም ለማቅረብ ዩናይትዶች አስበዋል ነገር ግን ባርሴሎናዎች ከተጫዋቹ ሽያጭ €60ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ዋጋ ይፈልጋሉፍ ሲል ከወደ ፈረንሳይ የሚታተመው le10sport አስነብቧል




አርሰናሎች ተጨማሪ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ወደ ገበያ ወተዋል የኒውካስትሉን ወጣት ግብ ጠባቂ ፍሬድ ኡድማንን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበዋል ከአርሰናል በተጨማሪ ሴልቲክም የግብ ጠባቂ ፈላጊ ነው ተብሏል አርሰናሎች ለልጁ ይፋዊ ጥያቄ አቅርበዋል




ዩናይትዶች ከክርስቲያን ኤሪክስን ወኪል ጋር ንግግር መጀመራቸው ተገለፀፖግባ የሚለቅ ከሆነ በምትኩ ዴንማርካዊውን አማካኝ ለማምጣት ይፈልጋሉ ተብሏል ተጫዋቹ ከስፐርስ ጋር የአንድ አመት ኮንትራት ይቀረዋል




ቶተንሀሞች የሪያል ቤትሱን አማካይ ጆቫኒ ሴልሶን ማስፈረም ቢፈልጉም ከዲያጎ ሲሞኒው አትሌቲኮ ማድሪድ እና ከናፖሊ ፉክክር ገጥሟቸዋል የስፔኑ ክለብ ልጁን ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው ይህንንም ተከትሎ ፈላጊ ክለቦቹ ተበራክተዋል ከሁሉም ግን ልጁ ወደ ቶተንሀም የማምራት እድሉ ሰፊ ነው




በርንማውዝ የሊቨርፑሉን የመስመር ተጨዋች ሀሪ ዊልሰንን ለማዘዋወር ለሊቨርፑል £25m ሊያቀርቡ ነው ዊልሰን በሳለፍነው የውድድር አመት በደርቢ እንዳሳለፈ ይታወሳል ከበርንማውዝ በተጨማሪ ኒውካስትል እና አስቶን ቪላ ፈላጊዎቹ ናቸው

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...