Wednesday, July 31, 2019

የረቡዕ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች



ጁቬንቱስ እና ማንችስተር ዩናይትድ በሉካኩ እና ዲባላ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል ዩናይትድ ከሉካኩ በተጨማሪ ገንዘብ እንደሚከፍል ተሰምቷል የዲባላ ወኪሎች ከዩናይትድ ሰዎች ጋር ተገናኝተው በግል ጥቅማ ጥቅም ዙሪያ ከስምምነት ደርሰዋል ሉካኩ እና ጁቬንቱስ ናቸው ሚቀሩት ሉካኩም ቀዳም ምርጫው ኢንተር ቢሆንም ወደ ጁቬ ለመሄድም ፍላጎት እንዳለው ታውቋል




ኢድሪስ ጋና አጉዬን ለፒኤስጂ የሸጡት ኤቨርተኖች በሱ ቦታ ላይ የሚጫወት ተጨዋች ለማስፈረም ተጠምዷል ከነዚህ ተጨዋቾች መካከል የሳውዛንብተኑ ጋቦናዊ ማሪዮ ሌሚና አንዱ ነው ይህንን ተጨዋች የማስፈረም  ፍላጎት አለ ከሳውዛንብተን ጋርም ይፋዊ ድርድር ጀምረዋል




አርተር ማሳኩ በዌስትሀም ኮንትራቱን አራዝሟል በኮንትራቱም በዌስትሀም እስከ 2024 የሚቆይ ሲሆን በተጨማሪም ኮንትራቱ ላይ ሁለት አመት መራዘም የሚችል ውልም ተካቶበታል




በአርሰናል ደጋፊዎች ብዙ ትችት እየደረሰበት የሚገኘው ሺኮድራን ሙስጣፊ አሁንም በኢምሬት ቆይቶ ቦታውን ማስጠበቅ ይፈልጋል አርሰናል ተጨዋቹን የመሸጥ አልያም ያለመሸጥ ምንም አይነት ፍላጎት እስካሁን አላሳየም ሞናኮ የተጨዋቹ ፈላጊ መሆኑ ይታወቃል አርሰናል ተጨማሪ ተከላካይ ካስፈረመ እንደሚለቁት ይጠበቃል




ቲያጎ ሞታ ፒኤስጂን ከለቀቀ ቡሀላ እስካሁን በትክክለኛ ተጨዋች ቦታው አልተተካም ነበር ብዙ ጊዜ ማርኪኒዮስ ይጫወት ነበር በመጨረሻም ፒኤስጂ ኢድሪስ አጋና አጉዬ ከኤቨርተን £29m ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል




ጣሊያናዊው ታማኝ ጋዜጠኛ ጂያን ሉካ ዲማርዚዮ  ትናንት ይፋ አንዳደረገው ከሆ ዩናይትድ የብሩኖ ፈርናንዴዝን እና የሀሪ ማጉዋየርን ዝውውር እንደጨረሰ ዘግቧል የማጉዋየር ዝውውር እልባቱን ያገኘ ሲሆን የፈርናንዴዝም ዝውውር ወደ መጠናቀቁ እየደረሰ ነው




ሳሚ ከዲራ ቀጣይ የአርሰናል ፈራሚ ሊሆን እንደ ሚችል ስካይ ስፓርት ኢጣሊያ ይዞ ወቷል ተጨዋቹ ከአርሰናል ጋር ተስማምቷል የሚል መረጃ ወቷል በመካከላቸው ያለው ልዩነት አርሰናሎች ደሞዝ እንዲቀንስ ይፈልጋሉ በጁቬንቱስ በአመት 6ሚዩ ነው ወደ አርሰናል ሲመጣ የ2አመት ኮንትራት ሚለጠው  ሲሆን አርሰናሎች አመታዊ ክፍያው 4ሚዩ እንዲሆን ይፈልጋሉ




ሀሜስ ሮድሪጌዝ በማድሪድ እንዲቆይ ፕሬዝዳንቱ ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ፍላጎታቸውን አሳይተዋል ግዴታም ነው ብለው 787 ቀናት ቡሀላ ከማድሪድ የቡድን አባላት ጋ ልምምድ ሰርቷል በጉዳት የታመሰውን የማድሪድ ቡድን ለመታደግ እንደ ሀሜስ አይፈለጉም የተባሉ ተጨዋቾችን ማቆየት እንዳማራጭ ተይዟል

1 comment:

  1. This is awesome.

    https://www.sportsviber.com.ng/2019/07/TransfersDybala.html

    ReplyDelete

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...