የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድየሌስተሩ ተከላካይ ሀሪ ማጉየር በ£80mየኦሌጉነር ሶልሻየር ሶስተኛ ፈራሚ በመሆን ኦልትራፎርድን ለመርገጥ መቃረቡን ታማኙው ጋዜጠኛ Gianluca Di Marzio,ዘግቧል
ባርሴሎና ማልኮምን ለዜኒትስበርግ ለመሸጥ ፍቃደኛ ሆነዋል ከክለቡም ጋር ተስማምቷል ተብሏል ባሳለፍነው ሳምንት ዶርትመንድ ይገባል ተብሎ በስፋት ቢወራም በመጨረሻም ወደ ሩሲያ ለማቅናት ተቃርቧል
ፓትሪክ ኩትሮኔ ዎልቭስን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሧል ለተጨዋቹ 18ሚዩ ይወጣበታል 4ሚዩ ደሞ እየታየ ይጨመራል ተጨዋቹ ስለ ዝውውሩ ሲጠየቅ የሚላን ደጋፊዎችን መሰናበት በጣም እጅግ ከባድ ነው ብሎ ለሁሉም አመስግኖ ለመልቀቁ ፍንጭ ሰቷል
ኒኮላስ ፔፔ አርሰናልን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሧል ተጨዋቹ አሁን የሚቀረው የጤና ምርመራ ብቻ ነው የሚቀረው በተለያዩ ክለቦች በጥብቅ ቢፈለግም በመጨረሻ ማረፊያ ኢምሬት ሊሆን ነው በ48ሰአታት ውስጥም ዝውውሩ ይፋ እንደሚደረግ ተሰምቷል
ቦሩሲያ ዶርትመንድ በቀጣይ አመት ማርዮ ጎትዘ ደሞዙን የማይቀንስ ከሆነ ክለቡን እንዲለቅ ፍቃድ እንደሚሰጠው ይፋ አድርጓል በሚቀጥለው የውድድር አመት ኮንትራቱ ይጠናቀቃል ከዛን ቡሀላ በዶርትመንድ መቆየት ከፈለገ የሚከፈለውን ዋጋ መቀነስ እንዳለበት በይፋ ተናግረዋል
ከባየርን ሙኒክ ከተለያየ ቡሀላ እስካሁን ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው ፍራንክ ሪቤር አዲስ ፈላጊ ክለብ መቷል እሱን ለማስፈረም ከዚ በፊት ሊቨርፑል እሱን ለማስፈረም እንደሚፈልግ እየተነገር ይገኝ ነበር አሁን ላይ ግን ፊዮሬንቲና እየፈለገው ይገኛል ለተጨዋቹም ጥያቄ እንዳቀረቡለት ታውቋል
ጁቬንቱስ ፓብሎ ዲባላን ለመሸጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ተጨዋቹ 100ሚዩ ነው እየተገመተ የሚገኘው ከሉካኩ ጋርም ገንዘብ ጨምሮ ከዩናይትድ ጋር ልውውጥ ሊያደርጉ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል
የሮሜሉ ሉካኩ ወደ ጁቬንቱስ ለመሄድ መቃረብን ተከትሎ ኢንተር ሚላን ፊታቸውን ወደ ሮማው ኤዲን ዤኮ አዙረዋል ኢንተር የመጀመሪያ ጥያቄያቸውን ለሮማ 13ሚዩ ቢያቀርቡም ውድቅ ሆኖባቸዋል
No comments:
Post a Comment