አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
የማድሪዱ ፕሬዝዳንት የጋሪዝ ቤልን ዝውውር አቋርጠውታል እንደምክንያትም የተቀመጠው ከቻይና የቀረበላቸው የዝውውር ጥያቄ አላሳመናቸውም የቻይናው ክለብ ቤልን በነፃ ነው የሚፈልገው ማድሪድ ደግሞ ከተጨዋቹ ገንዘብ ይፈልጋሉበሙኒክ በጥብቅ የሚፈለገውን ሊውርስ ሳኔ ወደ ሙኒክ ማቅናቱ አይቀሬ ሆኗል አሰልጣኙም ኒኮ ኮቫች በአስተያየታቸው ፍንጭ ሰተዋል ሲቲ ከልጁ እስከ £90m ይፈልጋሉ
አምና ከፈረንሳይ ወደ ስፔን አቅንቶ ማድሪድን የተቀላቀለው ማሪያኖ ዲያዝ በድጋሚ ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ ለሞናኮ ለመጫወት ከስምምነት እንደደረሰ ተሰምቷል ዲያዝ ወደ ሞናኮ ሚያቀናው በውሰት ነው
ኤቨርተኖች በይፋ ከጁቬንቱስ ጋር በዲባላ ጉዳይ ድርድር ጀምረዋል ኤቨርተኖች በይፋ ለልጁ ስንት እንዳቀረቡ ባይታወቅም ጁቬ ከልጁ ከ£36m በላይ ይፈልጋል
የጀርመኑ ሀምቡርግ ሀቪየር አማቺ የተባለ ከአርሰናል አንድ ተጨዋች አስፈርሟል ሀምቡርግ ለልጁ ለአርሰናል £2.25m + ተጨማሪ ክፍያ ይከፍላል
ኤሲሚላን ከፍላሚንጎ ሊዮ ዱአርቴን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሧል ኤሲሚላን ለ23 አመቱ ለብራዚሉ ክለብ €11m ለመክፈል ተስማምቷል ዱአርቴ በኤሲሚላን ለ5 አመት ለመቆየትም ተስማምቷል
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ትላንት ምሽት ጨዋታውን ለክለቡ ስፖርቲንግ
ሊዝበን ካደረገ በኋላ ወደ ደጋፊዎቹ በመዞር በእንባ ተለይቷቸዋል ምናልባትም መሰነባበቻ ጨዋታ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ማረፊያውም ማንችስተር ዩናይትድ ሊሆን ተቃርቧል
ኤቨርተን ኢድሪስ ጋና አጉዬ ከመርሲሳይዱ ክለብ የሚለቅ ከሆነ ተተኪ ለማግኘት ወደ ገበያው እንደሚወጡ ተሰምቷል ኤቨርተኖች እንደ አማራጭ የቸልሲውን ባካዮኮን ለማስፈረም ይፈልጋሉ
No comments:
Post a Comment