የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
የባርሴሎና ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ፔፕ ሴጉራል ክለቡን መልቀቃቸው ታውቋል በነሱ ምትክም የቀድሞ ተጨዋቻቸው ኤሪክ አቢዳል ሀላፊነቱን ተረክቦ ለመስራት ተስማምቷል ተብሏልባርሴሎናዎች ለኔማር መልክት ልከውለታል ኔይማር ባርሳን መቀላቀል ሚፈልግ ከሆነ ከማንኛውም ክለብ ጋር እንዳይነጋገር አስጠንቅቀውታል ምክንያቱም ባርሳዎች ያላቸው ገንዘብ ውስን ነው ከሌሎች ክለቦች ጋር ሚነጋገር ከሆነ ገንዘቡ ከፍ እንዳይልባቸው መፍራታቸው ታውቋል
ከፖርቶ ጋር የተለያየው ያሲን ብራሂሚ ወደ ኳታር አል ራያን አምርቷል አርሰናል በጥብቅ ይፈልገው ነበር በመጨረሻም ወደ ኳታር አምርቷል እንዲሁም የሀገሩ ልጅ ሜህዲ አቢዬድ ያለፈውን የውድድር ዘመን ለዲዮን ሲጫወት ነበር እዛው ፈረንሳይ ቆይቶ ለኖንት ፈርሟል
ማርኮ አሴንሲዮ ከዚ የውድድር አመት ውጪ መሆኑ ተሰምቷል ከአርሰናል ጋር በነበረው ጨዋታ ግብ አስቆጥሮ ተጎድቶ መውጣቱ ይታወሳል እናም አሁን ላይ ጉዳቱ ከዚህ አመት ውድድር ውጭ እንዳደረገው ታውቋል
ባርሴሎና ጁንየር ፊርፖ የሚባል የሪያል ቤትስ ተጨዋችን ለማስፈረም መቃረቡ ጂያሉካ ዲማርዚዮ መረጃ ይዞ ወቷል ይሄ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ባርሳዎች 27ሚዩ ለመክፈል ተስማምተዋል የጆርዲ አልባ ተጠባባቂ ይሆናል ብሏል
ሰሞኑ ዩናይትድ ኦባምያንግን ከአርሰናል ላይ መውሰድ ይፈልጋል የሚል መረጃ ሲወጣ ነበር እሱን ተከትሎ ኡናይ ኤምሪ ሲናገሩ በፍፁም ይሄ ሊሆን አይችልም ተጨዋቹን ማቆየት እንፈልጋለን በሁለቱም መስመሮች ብቸኛ አጥቂ እና ከሌላ አጥቂ ጋር መጫወት ይችላል ስለዚህ የማጥቃት መስመራችንን ማጠናከር እንፈልጋለን ስለዚህ አንለቀውም
ባየርን ሙኒኮች ሳኔን በጥብቅ ቢፈልጉትም እስካሁን ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ ተረጋግጧል ሲቲዎች ልጁን የመሸጥ ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ነገር ግን አሰልጣኙ ኒኮ ኮቫች በጣም የምንፈልገው ተጨዋች ነው ሁሉም ሰው እንደምንፈልገው ያቃል ነገር ግን እሱን ማግኘት ቀላል አደለም ጥረት ግን እያደረግን እንደሆነ ደጋፊዎቻችን እንዲያቁ እንፈልጋለን ብለዋል
እንደ ሌኪፕ ዘገባ ከሆነ ባርሴሎና ለኔይማር ዝውውር ከአራት ተጨዋቾች ሁለቱን እና ኩቲንሆ ራኪቲች ዴምቤሌ ኡምቲቲ እና ተጨማሪ ገንዘብ ከፍለን እናስፈርመው የሚል የዝውውር እቅድ አቅርበው ነበር ማድሪዶችም £90m እና ቤልን ሰተናቹ ኔማርን ስጡን ቢሉም ፒኤስጂዎች የዛሬ ሁለት አመት ያወጣነውን ገንዘብ ነው ምንፈልገው ብለው ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርገዋል
አርሰናል ዳኒ ሴባዮስን በውሰት ከሪያል ማድሪድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።መድፈኞቹ እንዳሳወቁት ከሆኑ ስፔናዊው አማካይ ኤምሬትስ የከተመው በአንድ አመት የውሰት ውል ሲሆን ከዚህ ቀደም አሮን ራምሴ ሚለብሰው የነበረውን 8 ቁጥር መለያም የሚለብስ ይሆናል።
ሴባዮስ ለአርሰናል ከብራዚላዊው ፈራሚ ጋብሬል ማርቲኔሊ በኋላ ሁለተኛው ፈራሚ መሆኑ ነው።
አርሰናል አሁን ሙሉ አይኑን ወደ ክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዘሃ እንደሚያዞር ይጠበቃል።
የኛ |ቁጥሮች|
ሜሲ እና ሮናልዶ በቁጥሮች ሲገለፁ ይህንን ይመስላል
አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር(የሪሐና ልጅ)
አሀዙ የተያዘው እስከ ሰኔ 30 ፥ 2011 እስካለው ዕለት ድረስ መሆኑን ውድ አንባቢዎች በቅድሚያ ከግምት እንድታስገቡት እንሻለን።
በአጠቃላይ ለክለብ እና ለሀገር
(የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ)
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 822 962
ለጎል አቀበለ 271 218
ግብ አስቆጠረ 671 689
በአጠቃላይ ለክለብ
(የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ)
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 687 804
ለጎል አቀበለ 231 190
ግብ አስቆጠረ 603 601
በሊግ ጨዋታዎች
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 452 544
ለጎል አቀበለ 162 134
ግብ አስቆጠረ 419 419
በአውሮፓ
(ሻምፒዮንስ ሊግ)
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 135 168
ለጎል አቀበለ 30 42
ግብ አስቆጠረ 112 127
በሌሎች የውስጥ ሊግ ጨዋታዎች
(ኮፓ ዴል ሬይ፥ስፓኒሽ ሱፐር ካፕ
ኤፍ ኤ ካፕ፥ሊግ ካፕ፥ኮምዩኒቲ ሺልድ
ክለብ ዎርልድ ካፕ፥UEFAሱፐር ካፕ)
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 100 92
ለጎል አቀበለ 39 14
ግብ አስቆጠረ 72 55
ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች (የሐገር)
(የወዳጅነት ጨዋታዎችን ይጨምራል)
ሜሲ ሮናልዶ
ተጫወተ 135 158
ለጎል አቀበለ 40 28
ግብ አስቆጠረ 68 88
No comments:
Post a Comment