የአርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
አልቤኒያዊው የናፖሊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ኤልሳይድ ሀልሳይ ከናፖሊ እንደሚለቅ የተጨዋቹ ወኪል ማሪዮ ጉድፍሬዲ በይፋ ተናግረዋል ናፖሊዎች አምስት የመስመር ተከላካዮች አሏቸው ስለዚህ ቦታ የለውም የሚል አስተያየት ሰቷል አ.ማድሪድ ቶተንሀም ጁቬ ሮማ የተጨዋቹ ፈላጊ ክለቦች ናቸው
የባየርን ሙኒኩ ፕሬዝዳንት ኦሊ ሆነሽ ከሙኒክ ፕሬዝዳንትነት እንደሚነሱ ተናግረዋል በሚቀጥለው ህዳር ወር በሙኒክ የፕሬዝዳንቶች ምርጫ ይደረጋል በዚ ምርጫ ላይ ለዳግመኛ መመረጥ እንደማይወዳደሩ ተነግሩዋል
ባርሴሎናዎች ከተጨዋቾች ሽያጭ 150ሚዩ ይፈልጋሉ ተብሏል በዝውውር መስኮቱ ለሁለት ተጨዋች ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣታቸው ይታወሳል እናም አምስት ተጨዋቾችን ለሽያጭ አቅርበዋል ራኪቲች ኩቲንሆ ማልኮም ራፊንሀአልካንትራ ኡምቲቲ ምናልባትም ስድስተኛ ተጨዋች ቪዳልም ሊሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል
ኔይማር ከግሎቦ ስፖርቴ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር በክረምቱ ከፒኤስጂ መልቀቅ መፈለጉ ግልፅ ነው ሲመልስ እንደ ማድሪድ ላለ ትልቅ ክለብ መጫወት እና የማድሪድን ማልያ መልበስ ክብር ነው ግን ህልሜ የነበረው በልጅነቴ የባርሴሎናን ማልያ መልበስ ነበር አሳክቼዋለው ግን ልል የፈለኩት ለማድሪድ መጫወት ፈልጋለው ሳይሆን ማድሪድ ከአለማችን ትልልቅ ክለቦች አንዱ ነው ፓሪስ ውስጥ መቆየት ሀሳብ እንዳለው ተናግሯል አሁን አይኔ ሁሉ ፓሪስ ላይ ነው በእግር ኳስ ነገ ሚፈጠረው አይታወቅም ብሏል
ብሩኖ ፈርናንዴዝን በተመለከተ አዲስ ዜና ወቷል ስፖርቲንግ ሊዝበን ሊሸጠው ባሰበው እና ዩናይትድ ሊገዛው ባሰበው ገንዘብ መካከል 7ሚዩ ልዩነት አለ ሊዝበኖች 62ሚዩ ሲፈልጉ ዩናይትዶች ደግሞ 55ሚዩ አቅርበዋል
በኬራን ቴርኒ የዝውውር ጉዳይ ላይ የሴልቲኩ አሰልጣኝ ኔን ሌነን አስተያየታቸውን ሰተዋል ይሄ ተጨዋች አርሰናሎች ምንፈልገውን ገንዘብ ስላልከፈሉ ልጁ እኛጋ ይቆያል ብለዋል ድርድሮች ቀጥለዋል በመጨረሻም መሳካቱ አይቀሬ ይሆናል
ኤቨርተኖች ዊልፍሬድ ዘሀን ለማስፈረም በዚ ሳምንት ለንግግር ይቀመጣሉ ተብሏል በአርሰናል በጥብቅ ቢፈለግም ኤቨርተን በመሀል ገብቶ ዝውውሩን ለመጨረስ እየሰሩ ይገኛል
ዳኔሌ ዴሮሲ ጫማ ሰቅላለው ሲባል ይሰማ ነበር አሁን ግን የቦካው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኒኮላስ ቡርዲሶ አሳምኖት አሁን ላቦምቦኔራ በሚባለው ስታድየም ውስጥ የመጫወት ህልም ነበረው ያንን ህልሙን ለማሳካት ወደ ቦካ ጁኒየርስ በይፋ አምርቷል
No comments:
Post a Comment