የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
ኢንተር ሚላን ማውሮ ኢካርዲን የሚፈልግ ክለብ 60ሚዩ መክፈል እንዳለበት ይፋ አድርገዋል ከቅድመ ውድድር ዝግጅት ከቡድኑ ጋር የማይገኘው ኢካርዲ ከሰሞኑ ወደ ናፖሊ ያመራል ቢባልም አንቾሎቲ ግን ልጁ ላይ ብዙም ፍላጎት እንደሌላቸው መሰማቱ ይታወሳል ሌላኛው ፈላጊ ክለብ ጁቬንቱስም ቢሆን እስካሁን በኢካርዲ ጉዳይ ዝምታን መርጠዋል
ጁቬንቱስ በቀጣይ ክለቡን ሊለቁ የሚችሉ ተጨዋቾችን በስም ይፋ አድርገዋል ሞይስ ኪን ፔሪን ከዲራን እና ማቲዩዲን ለመልቀቅ ዝግጁ ናቸው ሚፈልጋቸው ክለቦች ማስፈረም እንደሚችል አስታውቋል ፔሪን አስቶንቪላ ይፈልገዋል ሞይስ ኪንን ኤቨርተን ይፈልገዋል ሳሚ ከዲራም ወደ ቱርክ ሊያመራ ይችላል
ጁቬንቱስ ፖብሎ ዲባላን ለመሸጥ ተቃርቧል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው ቶተንሀሞች ዩናይትድን ተቀናቃኝ ሆነው ቀርበዋል ቶተንሀሞች በይፋ ለጁቬንቱሶች ፍላጎታቸውን ገልፀዋል ተብሏል ጁቬ ከበጨዋቹ £80m እየጠየቀ የሚገኘው በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለው ልዩነት ገንዘብ ብቻ ነው
ዩናይትድ እና ላዚዮ በሰርጂ ሚሊንኮቪች ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ደርሰዋል የተጨዋቹ ወኪል እና ዩናይትድ በግል ስምምነት ላይ ደርሰዋል በአመት 6ሚዩ እንዲከፈለውም ጭምር ታውቋል ዝውውሩም በቅርቡ ያልቃል የፖግባም መውጫ ጊዜ መቃረቡም ተነግሯል
ኤቨርተን የዊልፍሬድ ዘሀን ዝውውር ለመጨረስ እየሰራ ነው ኤቨርተን £55m አቅርቦ ከክርስትያል ፓላሴ ጋር እየተነጋገረ ነው በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለው ድርድር ጠንከር ያለ ነው ኤቨርተን ለልጁ ጠንከር ያለ ፍላጎት ስላለው እስከ £70m ድረስ ከፍ ሊያረግ ይችላል ፓላስ ለልጁ ከ£80-£100m ይፈልጋሉ
አርሰናል የቶተንሀሙን ቶቢ አልደርዊልድን ማስፈረም ይፈልጋሉ የ£25m የውል ማፍረሻ ትናንት የተጠናቀቀውን ይሄን ቤልጄማዊ የ30 አመት ተከላካይን በነፃ ለማስፈረም ይፈልጋሉ
ክርስቲያል ፓላስ በይፋ አንድሬ አየውን አስፈርመውታል አምና ከስዋንሲ ሲቲ በአንድ አመት የውሰት ውል አስፈርመውት በፓላስ እንደነበረ ይታወሳል በ3 አመት ውል ፓላስን ተቀላቅሏል
No comments:
Post a Comment