በእሳት የተፈተነው ወርቅ ኤልፌኔሚኖ
አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ለዛሬ ከእግር ኳስ ዲፓርትመንቶች አንዱ በሆነው የአጥቂ ስፍራ በመጫወት የዓለምን እግር ኳስ ተመልካች በጅምላ አጀብ ስላስባለው ድንቅ ብራዚላዊ አጥቂ ሮናልዶ ሊውስ ናዛሪዮ ዴሊማ ህይወት በአጭሩ የምንላችሁ አለን ውድ አንባቢዎች።
ሮናልዶ በሀገሩ ብራዚል የሚገኘውን ክሩዜሮ እግር ኳስ ክለብ ተቀላቅሎ የመጀመሪያው ቡድን ውስጥ ሲካተት ገና የ16 አመት ጎረምሳ ነበር።ከዚያም ከአንድ አመት በኋላ ወደ ሆላንዱ ክለብ ፒ.ኤስ.ቪ ኤንድሆቨን በማቅናት የአውሮፓ ህይወቱን አሀዱ አለ።
ከዚያም ድንቅ ጊዜን በአውሮፓ በማሳለፍ ገና በ20 አመቱ 1996 ላይ የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ በመመረጥ አጀብ አሰኘ።ሶስት ጊዜ ክብሩን በመቀዳጀትም በወቅቱ በታሪክ ሁለተኛው ተጨዋች ሆኖ ነበር።ሮናልዶ ባሎንዶርን ሁለት ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን በአለም ዋንጫም 15 ጊዜ ለሀገሩ ግብ በማስቆጠር 2014 ላይ ጀርመናዊው ሜሮስላቭ ክሎዝ ሪከርዱን እስኪሰብርበት ድረስ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱ በሱ እጅ ነበር።
መላጣው የጎል ማሽን 1996 ላይ ነበር ወደ ካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በወቅቱ ሪከርድ ዋጋ £19.5ሚሊየን የተዘዋወረው።ብራዚላዊው አጥቂ በባርሴሎና ቆይታው በ51 ጨዋታዎች 47 ጊዜ ግብ ማስቆጠር ችሏል።በዛን አመት ባርሴሎና ኮፓ ዴል ሬይ ፥ዩኤፋ ካፕ ዊነርስ ካፕን ሲያሸንፍ እንዲሁም ላሊጋውን ለጥቂት ሲነጠቅ የሮናልዶ ሚና አይተኬ ነበር።
ምንም እንኳን በባርሳ ድንቅ ጊዜያትን ቢያሳልፍም ክለቡ ግን እምብዛም ሊያቆየው አልቻለም።ከአንድ አመት በኋላ 1997 ወደ ጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ተዘዋወረ።ከዚያም በ1998ቱ የአለም ዋንጫ ለሀገሩ ብራዚል ትልቅ ስራ ሰራ።በውድድሩ አራት ግብ በማስቆጠርም የወርቅ ተሸላሚ ነበር።በዚያ የዓለም ዋንጫ እስከ ዛሬ ሁነኛ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ከፍፃሜው ጨዋታ ቀናት በፊት ተዝለፍለፎ በመውደቁ ምክንያት ሀገሩ በፈረንሳይ 3ለ0 ስትረታ መሲህ ሊሆንላት አልታደለም ነበር።
ጉዳት እና ፈተናዎቹ
ከዚያም በዚያኑ አመት ክረምት ላይ ወደ ሪያል ማድሪድ በመጓዝ ከሌሎች ጋላክቲኮስ ጋር በመሆን ስሙን በወርቅ ብዕር ማፃፉ አይዘነጋም።ከዚያም ከመጠን በላይ በመወፈሩ እና በአመጋገብ ስርዓቱ መዛባት ምክንያት 2011 ላይ ከእግር ኳሱ ዓለም ራሱን አግልሏን።
ሮናልዶ በአጠቃላይ የእግር ኳስ ህይወቱ 420 ጊዜ ግብን ማስቆጠር ችሏል።ለሐገሩ ብራዚልም በ98 ጨዋታዎች 62 ግቦችን ከመረብ በማዋሀድ ድንቅ ችሎታውን ለመላው የእግር ኳስ ተመልካች አሳይቷል።
No comments:
Post a Comment