ፖግባ ወደ ሪያል ማድሪድ የማቅናት ዕድሉ ሰፍቷል
ሪያል ማድሪዶች ፖል ፖግባን በዚሁ በክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደሚያዘዋውሩት ተስፋ አድርገዋል ይለናል ESPN በዘገባው።
ጋዜጣው በዘገባው እንዳተተው ምንም እንኳን ፖግባ በበርካታ የአውሮፓ ጉምቱ ክለቦች አይን ቢጣልበትም ፥ የሎስብላንኮዎቹ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ግን ክለቡ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ፈረንሳዊውን ኮከብ ስኳዱ ውስጥ እንዲያካትትለት ይሻል።
ሎስብላንኮዎቹ ማን ዩናይትድ የሚፈልገውን €180m (£162m/$200m) ለመክፈልም ጋሬዝ ቤልን እና ሀሜስ ሮድሪጌዝን ወደ ገበያ በማውጣት ጥቂት ገንዘብ ለማግኘት እና ፖግባ ዝውውር ላይ ገንዘቡን ለማዋል መላ የዘየዱ ሲሆን አሊያም ደግሞ ከሁለቱ አንዱን ተጨዋች ለቀያይ ሰይጣኖቹ በመስጠት የተጠየቀውን ገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን ለመቀነስ ነው ያሰቡት።
ፖግባ ከሪያል ማድሪድ በተጨማሪ በጁቬንትስ ፥ በባርሴሎና እንዲሁም በፔዤ በጥብቅ ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment