የቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
ዩናይትዶች ለማሰን ግሪንዉድ አዲስ ኮንትራት አቅርበውለታል 800ፓ ነበር በሳምንት የሚከፈለው በአዲሱ ኮንትራት ጥሩ ክፍያ እንደሚያገኝ ተሰምቷል ለዋናው ቡድን ሲጫወት በጨዋታ 5000ፓ ይከፈለዋል በፕሪሲዝን ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ እያሳየ የሚገኝ ሲሆን በዋናው ቡድንም ጥሩ ግልጋሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል
ዎልቭስ ፓትሪክ ኩትሮኔን ከኤሲ ሚላን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ኤሲሚላኖችም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቅ ይፈልጋሉ ዎልቭሶች ለጣሊያኑ ክለብ £16m አቅርበዋል ተጨዋቹንም የማስፈረም እድል እንዳላቸው ታውቋል
በጁቬንቱስ እንደማይፈለግ የተነገረው የ32 አመቱ ጀርመናዊ አማካይ ሳሚ ከዲራ በአርሰናል እየተፈለገ ይገኛል ባሳለፍነው የውድድር አመት ለጁቬ 10 ጨዋታዎችን ብቻ መጫወት የቻለው በክረምቱም ራምሴ እና ራቢዮ ጁቬን መቀላቀላቸው ተከትሎ ለመልቀቅ ተገዷል ከአርሰናል በተጨማሪ ጋላታሳራይም የልጁ ፈላጊ ነው
በቸልሲ አንድ አመት ኮንትራት የሚቀረው ብራዚላዊው ዊሊያን ተጨማሪ አንድ አመት ለማስፈረም ከስምምነት ደርሧል ለተጨማሪ ሁለት አመትም በብሪጅ እንደሚቆይ እርግጥ ሆኗል
ከአራት ወር በፊት ኮንትራቱን በጁቬንቱስ ያራዘመው ዳንኤል ሩጋኒ ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል እንደምክንያት የተቀመጠው በክለቡ በቀጣይ ካሉት ተከላካዮች ጋር ተፎካክሮ ቦታውን ማስጠበቅ እንደማይችል ስላመነ ነው በክረምቱ ጁቬዎች ከማቲያስ ዴላይት በተጨማሪ ሌላ ተከላካይ ማስፈረማቸው ይታወሳል
ቦሩሲያ ዶርትመንድ በባርሴሎና አስቸጋሪ የውድድር አመት ያሳለፈውን ብራዚላዊውን ማልኮምን ለማስፈረም መቃረቡ ተሰምቷል ዶርትመንድ ለተጨዋቹ ለባርሴሎና 42ሚዩ ለመክፈል ፍላጎት አላቸው ባርሳዎችም ልጁን አሳልፈው እንደሚሰጡዋቸው የጀርመኑ ክለብ ተማምነዋል
አምና በኤሲሚላን በውሰት አንድ አመት ያሳለፈውን የቸልሲ ተጨዋች ባካዮኮ ወደ ፒኤስጂ ያመራል ሲባል እንደነበር ይታወቃል አሁን ላይ ፒኤስጂዎች ፍላጎታቸውን አንስተዋል ምክንያቱም ቸልሲ በጨዋቹን ለመሸጥ እያመነታ ነው ሚገኘው የዝውውር እገዳ ስላለበት ላምፓርድ ልጁ ክለቡን ይልቀቅ አይልቀቅ የሚል ውሳኔ ላይ አልደረሰም
No comments:
Post a Comment