[ይፋዊ] አርሰናል ዳኒ ሴባዮስን አስፈረመ
አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር(የሪሐና ልጅ)
አርሰናል ዳኒ ሴባዮስን በውሰት ከሪያል ማድሪድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።መድፈኞቹ እንዳሳወቁት ከሆኑ ስፔናዊው አማካይ ኤምሬትስ የከተመው በአንድ አመት የውሰት ውል ሲሆን ከዚህ ቀደም አሮን ራምሴ ሚለብሰው የነበረውን 8 ቁጥር መለያም የሚለብስ ይሆናል።
ሴባዮስ ለአርሰናል ከብራዚላዊው ፈራሚ ጋብሬል ማርቲኔሊ በኋላ ሁለተኛው ፈራሚ መሆኑ ነው።
አርሰናል አሁን ሙሉ አይኑን ወደ ክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዘሃ እንደሚያዞር ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment