የሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
ኒውካስትሎች የክለቡን ሪከርድ በማሻሻል አዲስ የዝውውር ሰብሮ የሆፈንየሙን አጥቂ ዮሊተንን አስፈርሟል ለዝውውሩም £40m አውጥተዋል በኒውካስትልም የስድስት አመት ኮንትራት ፈርሟል
ዩናይትድ የላዚዮውን አማካይ ሚሊንኮቪች ሳቪችን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተሰምቷል እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ £67m በማውጣት የአምስት አመት ውል የሚፈርም ሲሆን ልጁ በዩናይትድ ብቃቱ እየታየ እንደሚጨመር ታውቋል ዝውውሩ ግን እውን የሚሆነው ፖል ፖግባ ማንችስተርን የሚለቅ ከሆነ ብቻ ነው
ቶተንሀም ሆላንዳዊውን አጥቂ ቪሰን ያንሰንን ለመሸጥ ከሜክሲኮ ክለብ ሞንቴሬ ጋር መስማማቱ ታውቋል 2016 ነበር ልጁን ከኤዜ አልካማር በ£17m ያመጡት የነበሩት ብዙ ያልተጠቀሙበትን ተጨዋች በመጨረሻም በ£10m የሜክሲኮውን ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል ቶተንሀምም ዝውውሩን ይፋ አድርጓል
ሊዮኔል ሜሲ ተቀጥቷል በኮፓ አሜሪካ በደረጃ ጨዋታ በቀይ ካርድ መውጣቱት ተከትሎ ከጨዋታው ቡሀላ ያልተገባ አስተያየት ሰቷል በሚል ኮምቦሜል ቅጣት አስተላልፎበታል የአንድ ጨዋታ እና የ1500 ዶላር ተጥሎበታል አርጀንቲና በኳታሩ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚያልፈው ይሆናል
አርሰናል በዩናይትድ የሚፈልገውን ኮትዲቫራዊውን ኮከብ ኒኮላስ ፔፔን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል የ24 አመቱ ፔፔ ሊልን ለቆ ዩናይትድ ሊገባ ነው ተብሎ ሲወራ ነበር ነገር ግን አርሰናል ዝውውሩ ሳይሳካ በመሀል በመግባት ልጁን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል
የአያክስ አምስተርዳሙ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ ገንዘብ የሚያቀርቡ ካሉ ተጨዋቾችን ለመሸጥ ዝግጁ ነን ብለዋል ፍራንክ ዲዮንግን እና ማቲያስ ዴላይትን በ75 በ75ሚዩ ሸጠዋል ሌላ አምስት ተጨዋቾችን ሽጠዋል አንዱን በነፃ እንዲሁም አራቱን ከ£10.5m በበለጠ ሽጠዋል ሁለቱን ኮከቦች በ150ሚዩ የሸጡት አያክሶች ሌላ ተጨማሪ አምስት ተጨዋቾችን 56.2ሚዩ በማውጣት አስፈርመዋል አሁንም ገዢ ከተገኘ እንደሚሸጡ አሰልጣኙ ተናግረዋል
አንድሬ ሲልቫ ወደ ሞናኮ ሊያመራ ከጫፍ ደርሶ ነበር ትናንት ወይ ዛሬ የሞናኮ ተጨዋች ይሆናል ሲባል ነበር ነገር ግን ዝውውሩ ጫፍ ከደረሰ ቡሀላ ውድቅ መሆኑ ተሰምቷል ምክንያቱ ደግሞ ተጨዋቹ በግል ጉዳይ ከሞናኮ ጋር አልተስማማም ሚል ነበር ሌሎች የፈረንሳይ ጋዜጦች ደግሞ በጤና ምርመራ ወቅት በተጨዋቹ ላይ ያጋጠመ ችግር አለ ሲሉ የጣሊያን ጋዜጦች ደግሞ በገንዘብ ጉዳይ እንዳልተስማማ እየፃፉ ነው ለሁሉም ግን ዝውውሩ በመጨረሻ ሳይሳካ ቀርቷል
የማንችስተር ዩናይትድ እና የፖግባ ጉዳይ በጣም አነጋጋሪ እየሆነ መቷል አዳዲስ ነገሮችም ዛሬ እየተሰሙ ይገኛሉ ሪያል ማድሪዶች ለልጁ 150ሚዩ ለመክፈል ይፈልጋሉ ዩናይትዶች ደሞ 200ሚዩ ካልተከፈለን ፖግባን አንለቅም ብለዋል
አስቶንቪላ ሙሀመድ ትርዝጌትን አስፈርሟል በአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻውን ግብ ያስቆጠረው አስቶንቪላ ተጨማሪ ተጨዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል
No comments:
Post a Comment