የሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
ናፖሊ ሀሜስ ሮድሪጌዝን ለማስፈረም አሁንም ተስፋ እንዳልቆረጠ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተናግረዋል ለዚህም ተጨዋች ክብር እንዳላቸው እና እስከ መጨረሻው ድረስ እሱን ለማስፈረም እንደሚጥሩ ተናግረው በማድሪድ እና በናፖሊ መካከል ንግግርም እንደቀጠለ ተናግረዋል
አዲሱ የጁቬ አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ በዚ የዝውውር መስኮት ተጨማሪ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ከሚፈልጉዋቸው ተጨዋቾች መካከል ቀዳሚው ፖል ፖግባ ነው በተጨማሪም የኢንተርሚላኑን ማውሮ ኢካርዲ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል
ሞናኮ የኤሲሚላኑን አንድሬስ ሲልቫን ለማስፈረም ደርሰዋል እንደ ጣሊያኑ ጋዜጣ ካልቺዮ መርካቶ ከሆነ ሞናኮ ሲልቫን ለማስፈረም ከጫፍ እንደደረሰ ፅፏል ሞናኮ ለልጁ £26.5m ለልጁ እንደሚከፍል ተረጋግጧል
የአፍሪካ ዋንጫ የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች የ21 አመቱ አልጄሪያዊው ቤናሴር ወደ ተለያዩ ክለቦች ያመራል ሲባል ቆይቶ ነበር በመጨረሻም ማረፊያው ኤሲሚላን ሊሆን ከጫፍ ደርሷል በተለይም ደግሞ የኢምፖሊው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አካርዲ ወደ ኤሲሚላን ለማምራት ከጫፍ መድረሱን አረጋግጠዋል
የጁቬንቱሱ ሞይስ ኪን ወደ ተለያዩ ክለቦች እንዲያመራ ጁቬንቱስ ፍላጎት አለው ተብሏል ነገር ግን ይሄንን ተጨዋች ሲሸጠው የመልሶ የመግዛት መብት በዝውውር አንቀፅ ውስጥ እንዲካተት ፍላጎት አለው እስከ £27m ማቅረብ የሚችል ክለብ ካለ ልጁን መግዛት ይችላል ነገር ግን ጁቬ በፈለገበት ሰአት £36m ማቅረብ ሚችል ከሆነ መግዛት ይችላል የሚል አንቀፅ እንዲካተት ይፈልጋል አርሰናል ቦሩሲያ ዶርትመንድ እና ኤቨርተኖች ፈላጊ ክለቦቹ ናቸው
ኮትዲቫራዊውንን ኒኮላስ ፔፔን ለማስፈረም ብዙ ክለቦች ፍላጎት አሳይተዋል ከሁሉም በላይ ፈላጊው የነበረው ናፖሊ ከገንዘቡ አንፃር ራሱን እንዳገለለ ተሰምቷል ምናልባትም አትሌቲኮ ማድሪድ አልያም ማንችስተር ዩናይትድ ቀጣይ ማረፊያው ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል ዩናይትዶች £70m የተገመተውን ፔፔን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንደጀመረም ታውቋል
ፒኤስጂዎች ኔይማርን ወደ ባርሴሎና እንዲያመራ አይፈልጉም ምክንያቱም ኔይማርን ሲያስፈርሙት በሁለቱ ክለቦች መካከል ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ገብተው ነበር ከማድሪድ ጋር ደግሞ ጥሩ ግንኙነት አላቸው ስለዚም ለባርሳ ከመሸጥ ይልቅ ወደ ማድሪድ እንዲሄድ ይፈልጋሉ
በአርሰናል በናፖሊ በሲቪያ ቫሊንሲያ ይፈለግ የነበረው ናቢል ፌኪር በመጨረሻም ወደ ስፔኑ ሪያል ቤትስ ለማምራት ተቃርቧል የሚል መረጃ ማርካ ይዞ ወቷል ሊዮን እና ሪያል ቤቲስ ተስማምተዋል ተጨዋቹም ወደ ስፔን ለማምራት ተስማምቷል
No comments:
Post a Comment