የዕለተ ሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
ፒ ኤስጂዎች ለኤቨርተኑ አማካይ ኢድሪሳ ጋና ጉዬ የተሻሻለ የዝውውር ሂሳብ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል የሊግ 1 ሻምፒዮኖቹ ለተጫዋቹ ዝውውር 30 ሚ.ፓ እና ለወደፊቱ የሚጨመር 10 ሚ.ፓ ለመክፈል አስበዋል
ዴቪድ ዴሂያ ኮንትራቱን ለማራዘም መስማማቱ ተዘገበ ዩናይትዶች ለተጫዋቹ በሳምንት 375,000 ፓውንድ የሚከፍሉት ሲሆን ተጫዋቹ የስድስት አመት ኮንትራት ማራዘሚያ እንደሚፈርም ይጠበቃል
ፖርቱጋላዊው አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝ ከሙኒከ መልቀቅ እንደማይፈልግ ተናገረ ተጫዋቹ ክለቡን ከመልቀቅ ይልቅ እዛው ሆኖ ለቦታው እንደሚፎካከር ተዘግቧል
የአትሌቲኮ ማድሪዱ የግራ ተመላላሽ ፊሊፔ ሉዊስ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ሊጫወት እንደሆነ ተዘገበ ባለ ልምዱ ብራዚላዊ ተጫዋች ወደ ፍላሚንጎ አቅንቷል ከልጅነቱ ጀምሮ ፍላሚንጎን እየደገፍኩ ነው ያደኩት ብሎ ሲናገር በተደጋጋሚ ይሰማ ነበር በመጨረሻም ህልሙን እውን አድርጓል
ባየርን ሙኒኮች አሪያን ሮበን እና ፍራንክ ሪበሪን ለመተካት አሁንም ገበያ ላይ ይገኛሉ የመጀመሪያ ታርጌታቸው የሲቲው ሊውሬ ሳኔ ሲሆን እሱ ማይሳካ ከሆነ ኦስማን ዴምቤሌን ከባርሳ ማምጣት ይፈልጋሉ በዴምቤሌ ዝውውር ዙሪያ ባርሳ ዴቪድ አላባን መፈለጉን ተከትሎ ዝውውሩ ውስጥ እሱን ለማካተት ይፈልጋሉ ሲቲንም ቢሆን በአላባ የቅያሪ የዝውውር ድርድር ለማድረግ ይፈልጋሉ
ሲቲዎች በድጋሚ የሀሪ ማጉዋየር ፈላጊ ሆነው ሊመጡ ነው የካምፓኒን ተተኪ እስካሁን ያላገኙት ሲቲዎች ድጋሚ ዩናይትድን መጫረት ሊጀምሩ ነው ለዚህም ይመስላል ማንጋላን እና ኦታሜንዲን በመሸጥ ማገዋየርን ማስፈረም የፈለጉት
የሊሉ ኒኮላስ ፔፔ ዩናትድን በጣም ይወዳል ዩናትዶችም በቅርብ
እየተከታተሉት እና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሊያመጡት አቅደዋል ሆኖም ግን ናፖሊ ዝዉዉሩን ለመጨረስ ገፍተዉ እየሄዱ ነዉ ይህ ኮትዲቫራዊ ኮከብ እስከ £70m ሚያወጣ ሲሆን ዩናይትድ የሉካኩን ዝውውር ሚያጠናቅቅ ከሆነ ኦልትራፎርድ መድረሱ የማይቀር ይመስላል
ኤዲ ኒኬታን በውሰት ለመልቀቅ እንዳላሰቡ የአርሰናሉ አሠልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ተናግረዋል በፕሪሲዝን ጥሩ ነገር እያሳየ የሚገኘው ተጫዋቹ በዚው ከቀጠለ በውሰት ከመስጠት ይልቅ በዋናው ቡድን የመሰለፍ ዕድል እንደሚሰጠው ተዘግቧል
No comments:
Post a Comment