የእሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም መሐመድ
ዩናይትዶች ለሮሜሉ ሉካኩ £54m ቀርቦለት ውድቅ አድርገዋል የቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ላይ እየተሰለፈ ማይገኘውን ሉካኩን የኢንተሩ አለቃ ኮንቴ በይፋ እንደሚፈልጉት ትናንት ከጨዋታው ቡሀላ ተናግረዋል ቸልሲ እያለው ፈልገው ነበር ጁቬ እያለው ላመጣው ተቃርቤ ነበር ብለዋል ዩናይትዶችም £54m ያንሰናል ብለዋልአስቶንቪላዎች ትሬዝጌ የሚባለውን በአፍሪካ ዋንጫ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ያደረገውን ግብፃዊ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል ይሄ ተጨዋች ለቱርኩ ካሲምፓሳ የሚጫወት ሲሆን አስቶንቪላ ዘጠነኛ ተጨዋቻቸውን ለማስፈረም ተቃርበዋል በክረምቱም £100m ለዝውውር አውጥተዋል
አርሰናል የሴንቲቲየኑን ሳሊባን ለማስፈረም ጣጣውን ጨርሷል ከቶተንሀም ጋር ፉክክር ውስጥ ቢገቡም ልጁ በመጨረሻም ምርጫው እዛው ሰሜን ለንደን ኢምሬት ሆኗል በቀጣዩ ማክሰኞም ወደ እንግሊዝ መቶ የህክምና ምርመራውን ያደርጋል
ቶማስ ቱሄል ስለኔይማር ተጠይቆ በመጪው ማክሰኞ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ጉዞ እናደርጋለን እሱም የቡድኑ አንድ አካል አርገን ይዘነው እኔዳለን ልምምድ ከኛጋ እየሰራ ነው ኔይማር የትኛውም አሰልጣኝ እንዲኖረው የሚመኘው ተጨዋች ነው ግን የክለቡን እና የሱን ነገር ግን ሁለቱ አካላት ናቸው መነጋገር ያለባቸው እኔ ቢቆይ ደስ ይለኛል ብሏል
ማርከሽ ቱራም የሊሊያም ቱራም ልጅ ወደ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባ የሚያደርገው ዝውውር ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል አዲሱ ክለቡ ሞንቼግላድባ ለልጁ 13ሚዩ የሚያወጣ ሲሆን ዝውውሩ እንደተጠናቀቀ ክለቡ ይፋ አድርገዋል
ሶሎሞን ሮንዶንን የለቀቁት ኒውካስትል ዩናይትዶች ሌላ አጥቂ ለማምጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል የቀድሞ ልጃቸውን አንዲ ካርሎን ከዌስትሀም ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ካሮሎም የሴባስቲያን ሀለር ወደ ዌስትሀም መምጣቱን ተከትሎ ክለቡን የመልቀቅ እድሉ ሰፊ ሆኗል
ዩናይትዶች ብሩኖ ፈርናንዴዝን በማስፈረም በሚካሄደው ሩጫ ውስጥ ከፒኤስጂ ፉክክር ገጥሞዋቸዋል ይህን ፉክክር ለማሸነፍ ይሰራሉ ተብሏል ዩናይትድ በፈርናንዴዝ ወኪል በኩል ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ በዚ ሳምንት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል
ጄሮሜን ቦአቴንግ ከአሜሪካ ወደ ሙኒክ ተመልሷል እንደ ምክንያት የቀረበው በግል ጉዳይ ነው ቢባልም ግን ከዝውውር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተነግሯል በጣሊያን እና በእንግሊዝ እንዲሁም በፈረንሳይ በትልልቅ ክለቦች ይፈለጋል በ£15m ለሚቀጥለው አመት ኮንትራቱ ከመጠናቀቁ በፊት ባየርን ልጁን ሊለቀው ይፈልጋል
ኤታናንፓዱ ወደ ጀርመን ሄዷል ላምፓርድ ይጠቀምበታል ቢባልም በአንድ አመት የውሰት ውል ወደ አርቢ ላይብዢክ ማምራቱን ሁለቱም ክለቦች አረጋግጠዋል
ሮማዎች ሌላኛ አዲስ ፈራሚ አግኝተዋል ጆርዳን ቬረቱት የሚባል ተጨዋች ከፊዮሬንቲና አስፈርመዋል ሮማ ለዝውውሩ 16ሚዩ የከፈለ ሲሆን አጠቃላይ ዝውውሩ እስከ 20ሚዩ እንደሚያወጣ ታውቋል
No comments:
Post a Comment