Monday, July 22, 2019

የማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

የማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
በክረምቱ አድራን ራቢዮትን እና አሮን ራምሴን በነፃ ዝውውር ወደ ክለባቸው ያመጡት ጁቬንቱሶች ፈረንሳዊውን አማካይ ብለስ ማቲዩዲን እንደሚሸጡት በይፋ ተናግረዋል የፈረንሳዩ ሞናኮም ልጁን ለማስፈረም የተሻለ እድል አለው ተብሏል




አርሰናሎች ለሴልቲኩ ግራ መስመር ተከላካይ ኬራን ትሪፒየር ሶስተኛ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል ካሁን በፊት አርሰናል £15m አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል ለሁለተኛ ጊዜ £25m አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል አሁን ላይ ደግሞ አርሰናሎች £30n ሊያቀርቡ ተዘጋጅተዋል ሴልቲኮች ከተጨዋቹ ዝውውር £45m እንደሚፈልጉ ባለፈው ሳምንት መናገራቸው ይታወቃል




ዩናይትዶች ሀሪ ማጉዋየርን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል ከዚህ በፊት ሌስተሮች ከ£80m በላይ መፈለጋቸው ይታወቃል በመጨረሻም ዩናይትዶች £70m በቅድሚያ የሚከፈል እንዲሁም £10 የተለያዩ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመክፈል በመስማማቱ ዝውውሩ ሊጠናቀቅ ከጫፍ ደርሱዋል




ጀምስ ሚልነር ከሊቨርፑል ጋር በኮንትራት ማደስ ጉዳይ ንግግር እንዳላረገ ተናገረ የሚልነር ኮንትራት በዚህ የውድድር አመት ሚጠናቀቅ ይሆናል እስካሁን ከሊቨርፑል ምንም አይነት ጥያቄ አልቀረበለትም የ33 አመቱ ሚልነር ምናልባታም ወደ ፒኤስጂ ሊሄድ እንደሚችልም ተነግሯል




ባሳለፍነው የውድድር አመት ድንቅ ጊዜን ያሳለፉት አያክስ አምስተርዳሞች ከአሜሪካ ክለብ ኤዲሰን አልቫሬዝ የተባለ ተጨዋች አስፈርመዋል ለልጁም አያክስ £15m ያወጡ ሲሆን ልጁም በአምስተርዳም አሬና እስከ 2024 የሚያቆየውን ውል ፈርሟል




ሎረንት ኮሸሌኒ ወደ ፈረንሳዩ ስታደሬስ ለመሄድ በግል  መስማማቱ ተስማምቷል በአርሰናል የአንድ አመት ኮንትራት ቢቀረውም አርሰናሎች አዲስ ኮንትራት አላቀረቡልኝም በሚል ወደ አሜሪካ አላቀናም ማለቱ  ይታወሳል ከስታደሬስ በተጨማሪ ቦርዶ እና ሊዮን ፈላጊ ክለቦች ነበሩ በመጨረሻም ግን ወደ ስታደሬስ ለመሄድ ተቃርቧል




በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቶተንሀምን ለቆ ወደ ሌላ ክለብ ያመራል የተባለው ቶቢ አልደርዊልድ ቶተንሀምን መልቀቅ እንደማይፈልግ ትናንት ከጁቬንቱስ ጨዋታ ቡሀላ ተናግሯል ከዚህ በፊት ከኤስሚላን የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ቢያደርጉም አሁን ላይ ግን ከሮማ ጋር ንግግር ላይ መሆናቸው ታውቋል




ማውሮ ኢካርድ ወደ ናፖሊ ለመሄድ ከካርሎ አንቾዎቲ ጋር ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ ኢንተር ሚላን በይፋ ተጨዋቹን እንደማይፈልገው መናገሩ ይታወቃል ስሙ ከጁቬንቱስጋም ሲያያዝም ቆይቷል በመጨረሻም ግን ማረፊያው ናፖሊ ሊሆን ተቃርቧል



ከቶተንሀም የቅድመ ውድድር ዝግጅት ውጭ የሆነው ዳኒ ሮዝ ወደ ጁቬንቱስ የሚያመራበት እድል አግኝቷል ከጁቬንቱስ በተጨማሪ ኒውካስትል ዩናይትድ ፒኤስጂ እና ሻልክ04 ፈላጊ ክለቦቹ ሲሆኑ ዳኒ ሮዝ በእንግሊዝ መቆየት የመጀመሪያ ምርጫው ነው

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...