Tuesday, July 23, 2019

የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

የማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናል ለክርስቲያል ፓላሱ ለዊልፍሬድ ዘሀ አዲስ የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል ካሁን በፊት ለተጨዋቹ £40m አቅርቦ በፓላስ ውድቅ እንደተደረገ ይታወሳል አርሴናል አሁን ላይ £55m እና ሬስ ኔልሰንን በውሰት ለፓላስ ለመስጠት አዲስ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል ፓላስ ለልጁ £80m እንደሚፈልጉ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል




ፈረንሳዊው የቸልሲ ኮከብ ኒጎሎ ካንቴ ለውድድር አመቱ መጀመርያ ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል ተጨዋቹ በጉልበት ጉዳት ከጃፓን ወደ ለንደን መመለሱ የሚታወስ ሲሆን ጉዳቱ ምናልባትም የውድድር አመቱ መጀመሪያ ከጨዋታ ያርቀዋል ቢባልም ቸልሲዎች እንደሚደርስላቸው ይፋ አድርገዋል




በመጨረሻም ናቢል ፌኪር የሪያል ቤትስ ተጨዋች መሆኑ ተረጋግጧል ቤትሶች ለዝውውሩ £17.75m ወጪ ያደረጉ ሲሆን £9.8m ደግሞ በቤቲስ የሚያሳየው አቋም እያሳየ የሚጨመር ይሆናል ሊዮን በቀጣይ ቤትሶች ፈኪርን ሚሸጡት ከሆነ ከሽያጩ 20% እንደሚያገኝ በስምምነቱ ውስጥ የሚገኝ ይሆናል




ኤሊፍ ኤልማስ ናፖሊን በይፋ ተቀላቅሏል ልጁ የፊነርባቼ ተጨዋች ነበር ናፖሊ ለተጨዋቹ 15ሚዩ እንደሚከፍል ተረጋግጧል ዛሬ በናፖሊ የህክምና ምርመራውን የሚያደርግ ነው




ቶተንሀም የሶልሴዎን ዝውውር ለማጠናቀቅ ተቃርቧል ተብሏል ቶተንሀም ለልጁ £45m ለመክፈል ተዘጋጅቷል ሪያል ቤትስ ከልጁ ዝውውር £60m ነበር የሚፈልገው ነገር ግን ፈኪርን ማግኘታቸውን ተከትሎ ለመልቀቅ ፈልገዋል ከዚህ ዝውውር ላይ የቀድሞ ክለቡ ፒኤስጂ ሲሸጥለት ስምምነቱ ውስጥ ልጁን ቤትስ የሚሸጡት ከሆነ 20% የዝውውር ዋጋ የሚያገኘው ይሆናል የቀድሞ ክለቡ ሮዛሪዮም ለፒኤስጂ የሸጠው ከዚህ ዝውውር £3% ከተጨዋቹ የሚያገኝ ይሆናል




ባርሴሎና የሊዮኔል ሜሲን ተጨማሪ ኮንትራት  ለማስፈረም እየተነጋገረ እንደሆነ ተሰምቷል የ32 አመቱ አጥቂ አንድ ተጨማሪ አመት ኮንትራት በባርሴሎና ሊፈርም እንደሚችል እየተነገረ ነው የሚገኘው የስንት አመት ኮንትራት እንደቀረበለት እና ምንያህል ገንዘብ እንደቀረበለት አልታወቀም




ኢንተርሚላን አርሰናል ለማውሮ ኢካርዲ ያቀረበውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተሰምቷል አርሰናል ኢካርዲን በኦባምያንግ ለመቀየር ቢፈልጉም ውድቅ ተደርጎባቸዋል ምክንያቱም ኢንተሮች ሉካኩን ከዩናይትድ ለማዘዋወር ስለሚፈልግ ከተጨዋች ይልቅ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ስላወቀ ኦባሚያንግን በመተው ለሉካኩ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረጉ ታውቋል




አንድሬ ሲልቫን ለሞናኮ ለመሸጥ ከጫፍ የደረሱት ኤሲሚላኖች የአትሌቲኮ ማድሪዱን አንጌል ኮሪያን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል ለዝውውሩም ኤሲሚላኖች £40m እና ቦነስ እንዳቀረበ ታውቋል ሲልቫን ለሞናኮ ሊለቁት የተቃረቡት ሚላኖች ኮሪያን ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸው ተነግሯል በቶተንሀም እና በወልቭስ ቢፈለግም ማረፊያው ሚላን ሊሆን ተቃርቧል




ሰሞኑ ከቻይና ክለቦች ጋ ስሙ እየተነሳ የሚገኘው ጋሪዝ ቤል በመጨረሻም ማረፊያው ቻይና ሊሆን ተቃርቧል ከአንድ የቻይና ክለብ ሳምንታዊ £1m እንደቀረበለት ይታወሳል ሪያል ማድሪድ የቻይናው ክለብ ይሄን ተጨዋች ማስፈረም የሚፈልግ ከሆነ ምንም አይነት የዝውውር ሂሳብ እንደማይፈልግ ይፋ አድርገዋል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...