Tuesday, July 23, 2019

በእግር ኳስ ታሪክ በርካታ ዋንጫዎችን ያሳኩ 10 የአውሮፓ ክለቦች ዝርዝር

በእግር ኳስ ታሪክ በርካታ ዋንጫዎችን ያሳኩ 10 የአውሮፓ ክለቦች ዝርዝር

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር(የሪሐና ልጅ)

ውድ አንባቢዎች ይህ አሀዝ የሚያጠቃልለው ይፋዊ ዋንጫዎችን ሲሆን የተካተቱት ክለቦችም በአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች የሚገኙ ክለቦች መሆናቸውን በቅድሚያ ማሳወቅ እንሻለን።




10.አትሌቲኮ ማድሪድ
በአውሮፓ ከሚገኙ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች ከፍተኛ ዋንጫ በማሳካት አስረኛውን ደረጃ የያዘው የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ሲሆን 32 ዋንጫዎችን አሳክቷል።



9.ኢንተር ሚላን
በጣሊያን ከሚገኙ ሕያላን ክለቦች አንዱ የሆነው ኢንተር ሚላን በ39 ዋንጫዎች ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።



8.አርሰናል
የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል 45 ዋንጫዎችን በማሳካት ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።



7.ኤሲ ሚላን
በቀደመው ዘመን የስኬት ማማ ላይ ደርሶ የነበረው ኤሲ ሚላን ደግሞ በ48 ዋንጫዎች ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።



6.ሊቨርፑል
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል 59 ዋንጫዎችን በማሳካት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።



5.ጁቬንትስ
በተከታታይ ሴሪ ኤው ላይ የነገሰችው አሮጊቷ በ64 ዋንጫዎች አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።



4.ማን ዩናይትድ
ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን አብዮት በኋላ የስኬት ማማ ላይ የወጣው ማን ዩናይትድ በ66 ዋንጫዎች አራተኛ ደረጃን ይዟል።



3.ባየርን ሙኒክ
የባቫሪያው ክለብ ባየርን ሙኒክ 70 ዋንጫዎችን በማሳካት ከአውሮፓ ክለቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።



2.ሪያል ማድሪድ
በአውሮፓ ስኬታማ ከሆኑ ኋያላን ክለቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ በ90 ዋንጫዎች የተቀመጠው ሪያል ማድሪድ ነው።



1.ባርሴሎና
ከአውሮፓ አምስት ታላላቅ ሊጎች አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በ93 ዋንጫዎች ነው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...