Wednesday, July 24, 2019

የረቡዕ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

የረቡዕ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ -ኢብራሒም ሙሐመድ
ባርሴሎና ዳቪድ አላባን ከባየርን ሙኒክ ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱ ተነግሯል በበርካታ አማራጭ መጫወት የሚችለውን አላባን ለማስፈረም ባርሴሎና ዝውውሩን ገፍተው እንደሄዱበት ታውቋል




የቤል መውጣት ወደ መቃረቡ ተከትሎ ሪያል ማድሪድ እና ፖግባ ስማቸው መነሳት ጀምሯል ማድሪዶች አሁንም ፖግባን አልተውትም የቤል መውጣት ብቻ ነው ሚጠበቀው ምናልባትም ቤል ከወጣ ቡሀላ £150m በማውጣት ፖግባን ማስፈረም ይፈልጋሉ




በክረምቱ የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሮማዎች ሱሶን ከኤሲሚላን ማስፈረም ይፈልጋሉ ተብሏል እንደ አማራጭ ደግሞ የዋትፎርዱን ጄራርድ ዴሌፊውን ፈልገዋል ሮማ ለዴሌውን 15ሚዩ እና ሮበን ኦልሰንን በተጨማሪ ሊሰጥ እያሰበ ነው ተብሎዋል




በዩናይትድ የሚፈልገው ብሩኖ ፈርናንዴዝ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል በቅርቡ የዩናይትድ እና የብሩኖ ፈርናንዴዝ ጉዳይ እልባቱን ያገኛል ተብሏል ዩናይትድ ለልጁ እስከ 62ሚዩ ያሶጣቸዋል ተብሏል




ናፖሊ የፊነርባቼውን አማካይ ኤልፍ ኤልማስን በ16ሚዩ አስፈርሟል የ19 አመቱ አማካይ የኢማዱ ዱዋራን ክፍት ቦታ ይሸፍናል ተብሏል ዱዋራ ወደ ሮማ እንደሄደ ይታወሳል ናፖሊ በቀጣይ ሀሜስ ሮድሪጌዝን ለማስፈረምም እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል




ሎረንት ኮሸሌኒ ወደ ሬንስ ሊያመራ እንደሚችል የክለቡ ፕሬዝዳንት ኦሊቭሬንታንት ተናግረዋል ከዝውውሩ ጋር በተያያዘ ሲናገሩ እየተቃረበ ነው ማለት ይቻላል ብለዋል ተስማምተዋልም የሚሉ መረጃዎች ወተዋል ከሬን ጋር አሁን የሚቀረው ከአርሰናል ጋር ብቻ ነው




ቨርጅል ቫንዳይክ የባላንዶር ሽልማት ካገኘው ህልሜ እውን ሆኗል የሚል አስተያየቱን ሰቷል ከሊቨርፑል ጋር የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳው እንዲሁም ሀገሩን ለኔሽን ካፕ ፍፃሜ ማድረሱ ይታወሳል




ኢንተር ሚላን ሉካኩን ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት እንዳቀዘቀዘው ተሰምቷል ሚላኖች በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም በመሀከላቸው ያለው የገንዘብ መጠን እንዳላስማማቸው የሚታወስ ነው ኢንተሮች አሁን ፊታቸውን ወደ ሮማው ኤዴን ዤኮ እንዳዞሩ ተሰምቷል




የባየርን ሙኒኩ ግብ አዳኝ ሮበርት ሎዋንዶስኪ ማልስ ሀመልስን ወርፎታል ሀመልስ ከሙኒክ የለቀቅ ፉክክርን ፈርቶ ነው ብሏል ወደ ዶርትመንድ ለመመለስ ፈልጎ ሳይሆን ተጠባባቂ ወንበር ላይ መቀመጥ ስለማይፈልግ ነው ብሏል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...