የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
በቅደመ ውድድር ጨዋታዎች ዛሬ ሁለቱ የጣሊያን ጉምቱ ክለቦች ጁቬንትስ እና ኢንተር ሚላን ተጫውተው አሮጊቷ በፍፁም ቅጣት ምት 4ለ3 በሆነ ውጤት ረትታለች።በጨዋታው አዲሱ ፈራሚ ማቲያስ ደ ላይት ራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደግሞ የጁቬንትስን ግብ በድንቅ ቅጣት ምት አስቆጥሯል።(Goal)
በቅድመ ዝግጅት ጨዋታ አደገኛ ጉዳት ያጋጠመው ማርኮ አሴንሲዮ እስከ ቀጣዩ አመት ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ክለቡ ሪያል ማድሪድ ይፋ አድርጓል።
(AS)
ማን ዩናይትድ ዴንማርካዊውን የአጥቂ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከቶተንሃም ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ይገኛል።ዴይሊ ሜል በዘገባው እንዳተተው ከሆነ ቀያይ ሰይጣኖቹ የኮንትራቱን የመጨረሻ ሲዝን በስፐርስ እያሳለፈ ያለውን ድንቅ አማካይ ለማዘዋወር ያቀረበው £70 ሚሊየን ነው።
ሪያል ማድሪድ፥ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድም የልጁ ቀንደኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(Daily Mail)
ፓሪሰን ዤርመን ኢድሪሳ ጋና ጉዌን ከኤቨርተን ማስፈረሙን በዚሁ ሳምንት መባቻ ይፋ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።የፓሪሱ ክለብ ከአማካዩ ጋር ለወራት ስሙ ሲያያዝ የሰነበተ ሲሆን ባሳለፍነው የጥር ወር የዝውውር መስኮትም ሊያስፈርመው ሞክሮ በለስ አልቀናውም ነበር።
ሆኖም በስተመጨረሻ ተጨዋቹን ፓርክ ደ ፕሪንስ ለማክተም ፔዤ £28 ሚሊየን ለኤቨርተን አቅርቦ ለስምምነት ላይ ደርሷል።
(Sky Sports)
አርሰናል አራት ተጨዋቾችን ወደ ኤምሬትስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።እነዚህ ተጨዋቾች ዊልፍሬድ ዘሃ፥ኬሬን ቴርኒ፥ዳኒ ሴባዮስ እና ዊልያም ሳሊባ ናቸው።
የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ አንስቶ እምብዛም ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑት መድፈኞቹ በተለይም ዳኒ ሴባዮስን እና ዊልያም ሳሊባን የማዘዋወር ዕድላቸው የሰፋ ነው ተብሏል።
(Goal)
ዳኒ አልቬዝ ከፔዤ መልቀቁ እርግጥ መሆኑን ተከትሎ ኔይማር በድጋሚ ከክለቡ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቷል።ወትሮም ቢሆን ከፓሪሱ ክለብ ለመልቀቅ እንደሚሻ ያልደበቀው ኔይማር የሀገሩ ልጅ ከክለቡ መሰናበት ደግሞ ይበልጥ ከክለቡ እንዲለቅ ምክንያት ይሆነዋል ተብሏል።
Express (via L'Equipe)
ቪክቶር ሊንደሎፍ ሀሪ ማጉዌር ወደ ማን ዩናይትድ ቢመጣ እንደሚደሰት ተናገረ።ማን ዩናይትድ ማጉዌርን በተደጋጋሚ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ሲሆን እንግሊዛዊው ተከላካይ ወደ ኦልድ ትራፎርድ የሚመጣ ከሆነ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ከኤሪክ ቤይሊ፥ስሞሊንግ እና ፊል ጆንስ ጋር እየተፎካከረ ላለው ሊንደሎፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚሆንበት አሌ የማይባል እውነት ነው።
(Goal)
No comments:
Post a Comment