Monday, July 8, 2019

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች



የኒውካስትል ዩናይትዱ ባለቤት ማይክ አሽሊ ለሚቀጥለው
ሲዝን አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም እየኳተኑ ነው።በደጋፊዎቹ እጅግ የሚጠሉት አሽሊ እቅዳቸው በአሁኑ ሰዓት በሬንጀርስ በማሰልጠን ላይ የሚገኘውን የቀድሞውን የሊቨርፑል ሌጀንድ ስቴቨን ዤራርድ መሾም ነው።
(Mirror)





የፖል ፖግባ ጉዳይ አሁንም በስፋት እየተነሱ ካሉት ዜናዎቹ ውስጥ ነው።ከማን ዩናይትድ መውጣቱ አይቀሬ የሚመስለውን ፈረንሳዊ አማካይ ለማዘዋወር ጁቬንትስ የተሻሻለ €120ሚ. ማቅረቡ ተገልፇል።የ26 አመቱን አማካይ ወደ ቀድሞው ቤቱ መመለስ የማውሪዚዮ ሳሪ ትልቅ ህልም ነው።
(Times - subscription required)




ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴሄያ በማን ዩናይትድ ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ሊፈራረም ነው።በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ካለፉት ሲዝኖች አንፃር ዘንድሮ ደካማ አቋም ያሳየው የ28 አመቱ የግብ ዘብ በአዲሱ ኮንትራቱ ሳምንታዊ £350,000 እንደሚከፈለውም ነው የተገለፀው።
(Mirror)



የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ዠርደን ክሎፕ ወኪል ጀርመናዊው የጌጌም ፕሬሲንግ ሊቀ-ጠበብት አንድ ቀን የጀርመንን ብሄራዊ ቡድን የማሰልጠን ህልም አላቸው ሲል ተናገረ።ወኪሉ እንዳለው ከሆነ ክሎፕ በአሁኑ ሰዓት በሊቨርፑል ባላቸው ቆይታ ደስተኛ ቢሆኑም ለወደፊት ሀገራቸውን ማሰልጠን ውጥናቸው ነው ብሏል።
(Welt - in German)



ባርሴሎና በዌስት ብሮም ያለው ኮንትራት የተገባደደውን የ16 አመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ሎዊ ቤይሪ ማስፈረም ችሏል።ታዳጊው አጥቂ በፓሪሰን ዤርመን በጥብቅ ይፈለግ ነበር።
(Sun)








አሌክሳንደር ሚትሮቪች በፉልሀም እስከ 2024 የሚያቆየውን አዲስ የ 5 አመት
ውል ተፈራረመ [Fulham FC]



የቀድሞ የዩናይትድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከቻይናው ክለብ ግዋንግዙ
ኤቨርግራንዴ የቀረበለትን ከፍተኛ የእናዘዋውርህ ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል
ከፍተኛ የሚባል የ88ሚፓ ክፍያ ቢቀርብላቸውም ውድቅ አድርገዋል ጥያቄውን
ቢቀበሉ ኖሮ ከፍተኛ የአለማችን ተከፋይ አሰልጣኝ ይሆኑ ነበር[Daily Mail]



ፒ ኤስ ጂዎች የ አያክስ አምስተርዳሙን ሚሼል ባከርን በነፃ የ4 አመት ውል
አስፈርመውታል [PSG]



ማንቸስተር ሲቲዎች የተከላካይ ክፍላቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የበርንማውዙን
ናታን አኬን ማስፈረም ይፈልጋሉ። ዝውውሩ በአረቦች ለሚመራው ክለብ እስከ
40 ሚሊየን ፓውንድ ሊያስወጣ እንደሚችል ተዘግቧል [Sunday Mirror]



አትሌቲኮ ማድሪዶች የቤኔፊካውን ኢቫን ሳፖኒክ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል
ተጫዋቹ ወደ ማድሪድ ከተማ አቅንቶ ዛሬ ሜዲካሉን የሚያደርግ ይሆናል [AS]




አዮዜ ፔሬዝ ከ ኒውካስትል ዩናይትድ ወደ ሌይሰስተር ሲቲ የሚያደርገውን
ዝውውር ለማጠናቀቅ የህክምና ምርመራውን አልፏል [sky sport]



ዚነዲን ዚዳን ፖል ፖግባ ለዩናይትድ የዝውውር ጥያቄ እንዲያቀርብ ይፈልጋል
ማድሪዶች ፖግባ የመጨረሻ የልቀቁኝ ጥያቄ በግልፅ ለዩናይትድ እንዲያቀርብ
ይፈልጋሉ[Mundo Deportivo]






ቤኔፊካዎች ራውል ዲ ቶማስን ከ ሪያል ማድሪድ ማስፈረማቸውን ይፋ
አድርገዋል ዝውውሩ እስከ 18 ሚሊየን ፓውንድ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል
[Sport Lisboa e Benfica]


የዌስትሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ማርኮ አርናቶቪች ወደ ቻይና ማምራቱ
ተረጋግጧል የ30አመቱ አጥቂ ለሻንጋይ ሳይፒጂ ነው የፈረመው ለዝውውሩም
22.4ሚፓ ተከፍሎለታል[Sky Sport]



ሲቪያዎች የማርሴዩን ተጫዋች ሉካስ ኦካምፖስን ወደ 11.7 ሚሊየን ፓውንድ
በሚጠጋ ገንዘብ በ 5 አመት ውል ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል [Sevilla
FC]




አትሌቲኮ ማድሪዶች የምንግዜም የክለባቸውን ውዱ ፈራሚ ጆአኦ ፊሊክስን ዛሬ
ከሰአት በይፋ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከክለቡ ደጋፊዎች በይፋ እንደሚያስተዋወቁ
ታውቋል




ዌስትሀም ዩናይትዶች የአርናቶቪችን ተተኪ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል
የሴልታቪጎውን አጥቂ ማክሲ ጎሜዝን ውል ማፍረሻውን 44.8ሚፓ ለመክፈል
መስማማታቸው ተሰምቷል[The Sun]


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...