Saturday, July 6, 2019

የቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

የቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                          አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር(የሪሃና ልጅ)




ሜሱት ኦዚል ወደ ትውልድ ሀገሩ ቱርክ ክለብ ፌነርባቼ በውሰት ለመዘዋወር ተቃርቧል።መድፈኞቹ የ30 አመቱን ጀርመናዊ ኢንተርናሽናል ለመልቀቅ ያቀዱት የተጨዋቹ ሳምንታዊ ደሞዝ ከሌሎች ተጨዋቾች ጋር ያለው ልዩነት እጅግ የተጋነነ በመሆኑ ነው ተብሏል።
(Futbol Arena)





ቶተንሃም እና ሮማ የሪያል ማድሪዱን ማሪያኖ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ከሊዮን ሎስብላንኮዎቹን ከተቀላቀለ አንስቶ በቋሚነት ለመሰለፍ የተቸገረው ማሪያኖ በሳንቲያጎ በርናቢዮ ለአራት ተጨማሪ አመታት የሚያቆይ ኮንትራት ቢቀረውም ክለቡን ለመልቀቅ የደረሰ ይመስላል።
የ25 አመቱን ተጨዋች ሮማ በውሰት ለመውሰድ ቢፈልግም ማድሪድ ተጨዋቹን በቋሚነት መሸጥ ስለሚሻ የእንግሊዙ ቶተንሃም ዝውውሩን የማገባደድ የሰፋ ዕድል አለው።
(AS)






(ይፋዊ) ሮበርት ሎዋንዶልስኪ በባየርን ሙኒክ ለተጨማሪ አራት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል።
ስሙ በስፋት ከዝውውር ጋር ሲገናኝ የነበረው ፖላንዳዊው የጎል ማሽን በባቫሪያ ለተጨማሪ አመታት ለመሰንበት መስማማቱ እሙን ሆኗል።
( Sky Sport)






አርሰናል ካሉን ቼምበርስ አሊያም ሙሀመድ ኤልኒኒ አሊያም ካርል ጄንኪንሰንን ለክሪስታል ፓላስ በማቅረብ ዊልፍሬድ ዛሃን ወደ ኤምሬትስ ለማምጣት ጥረት ማድረግ ጀምሯል።
አርሰናል £40ሚ  ለክሪስታል ፓላስ ያቀረበ ቢሆንም ፓላስ በአንፃሩ £80ሚ ካልቀረበ አንገቴን ለቢላ ማለቱን ተከትሎ ነው አርሰናል ከገንዘብ በተጨማሪ ተጨዋቾችን ለክለቡ በምልጃ መልክ ያቀረበው።ፓላስ ምናልባትም የአሮን ዋን ቢሳካን ቦታ ለመተካት ካርል ጄንኪንሰንን ከመድፈኞቹ ሊወስድ ይችላልም ተብሏል።
(Mirror)






ጁቬንትስ ሮሜሮ ሉካኩን ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ስሙ በስፋት እና በተደጋጋሚ ከኢንተር ሚላን ጋር ሲያያዝ የሰነበተው ቤልጄሚያዊ ኢንተርናሽናል ወደ አሮጊቷ ለመሄድ ተቃርቧል ሲል ታማኙ ጣሊያናዊ ጋዜጠኛ ጂያንሉካ ዲማርዚዮ ተናግሯል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ ባሳለፍነው አመት በ32 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ ላሳረፈላቸው አጥቂ £75ሚ. ከቀረበልኝ ለመልቀቅ ምን ገዶኝ ብለዋል።
(gianlucadimarzio)






ሀሜስ ሮድሪጌዝ ሪያል ማድሪድ ለቅደመ ውድድር ዝግጅት ወደ ካናዳ በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ስሙን ባለማካተቱ ወደ ናፖሊ መሄዱ አይቀሬ ነው የሚለውን ዜና ሚዛን እንዲደፋ አድርጎታል።ዚነዲን ዚዳን ለተጨዋቹ ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ የተገለፀ ሲሆን ኮሎምቢያዊውም አጥቂ ወደ ማድሪድ መመለስን አይሻም።ይህም ያለፉትን ሁለት አመታት በውሰት በባየር ሙኒክ ያሳለፈው የ27 አመቱ አጥቂ ወደ ኔፕልስ ይሄዳል ለሚለውን ዜና እሙንነት አይቀሬ መሆን  ያሳያል ተብሏል።
(MARCA)





ሌስተር ሲቲ የ22 አመቱን ቤልጄሚያዊ ዮሪ ቴልማስ በክለቡ ሪከርድ ዋጋ ከሞናኮ ለማዘዋወር ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር ድርድር ጀምሯል።አማካዩ ባሳለፈነው አመት ለግማሽ አመት በኪንግ ፓወር በውሰት መጫወቱ ይታወሳል።
(Leicester Mercury)







ቶተንሃም በዘንድሮ የታዳጊዎች የአለም ዋንጫ  ድንቅ አቋሙን ያሳየውን የ22 አመቱን ስፔናዊ አማካይ ዳኒ ሴባዮስ ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል ፥ የአውሮፓው የወቅቱ ሻምፒዮን ሊቨርፑልም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(AS)







ማን ዩናይትድ የኒውካስትል ዩናይትዱን እንግሊዛዊ አማካይ ሲን ሎንግስታፍ ለማዘዋወር ጥረት ጀምሯል።አዳዲስ ተስፈኛ ወጣቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ላይ ያለው ኦሊ ጉናር ሶልሻየርም ተጨዋቹን በጥብቅ ይፈልገዋል።
(Sky Sports)





በበርካታ ክለቦች በጥብቅ እየተፈለገ ያለው ማቲያስ ደ ላይት አሁንም ማረፊያው የት እንደሚሆን በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።የ19 አመቱን ሆላንዳዊ ተከላካይ ለማዘዋወር በአሁኑ ሰዓት ፓሪሰን ዤርሜን እና ማን ዩናይትድ ትልቅ ዕድል አላቸው።
(European football expert Julien Laurens, via Express)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...