ዕለተ ሀሙስ ምሽት የወጡ የሀገር ውስጥ እንዲሁም የባህር ማዶ ስፖርታዊ መረጃዎች
አዘጋጅ እና አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
⇉በዘንድሮ አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሰናበቱት ሶስቱም ክለቦች በስተመጨረሻ ታውቀዋል።አስቀድሞ መውረዱን ካረጋገጠው ደደቢት ጋር የሚወርዱት ሁለት ክለቦችን ለማወቅ እስከትናንትናዋ ዕለት ድረስ የእግር ኳስ ቤተሰቡ ለማወቅ ጊዜ የወሰደበት ቢሆንም በስተመጨረሻ እነዚህ ሁለት ክለቦች አንጋፋው ክለብ መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ መሆናቸው እውን ሆኗል።
በዚህም መሰረት ደደቢት ፥ መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ ከ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሰናበታቸው ከወዲሁ ተረጋግጧል።በቀጣዩ አመት እነዚህን ክለቦች በመተካት ወደ ሀገሪቱ ቁንጮ ሊግ የሚመጡት ወልቂጤ ከነማ ፥ ሀዲያ ሆሳዕና እና ሰበታ ከነማ መሆናቸው ከሳምንታት በፊት መረጋገጡ የሚታወስ ነው።
⇉ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ጋር ያለው እሰጣ እገባ አንጋፋውን ክለብ ከሊጉ እንዲወጣ ምክንያት ሊሆነው ይችላል የሚል ሀሳብ በበርካታ የእግር ኳስ ቤተሰብ ዘንድ እየተነሳ ይገኛል።የ83 አመታት ዕድሜ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ትናንት ከፋሲል ከነማ ጋር ላለበት ጨዋታ ከዚህ ቀደም የነበረውን መርሃ ግብር ሳያደርግ ወደ ጎንደር እንደማይጓዝ ቀድሞ ለፌድሬሽኑ ያሳወቀ ቢሆንም አወዛጋቢው ፌድሬሽን ግን ክለቡ በፎርፌ እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
ይህንን ውሳኔም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ውሳኔው ተገቢ እንዳልሆነ እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እንደሚቆም አስታውቋል።ሁለቱ ሰፊ ህዝባዊ የደጋፊ መሰረት ያላቸው የመዲናዋ ብሎም የሀገሪቱ ጉምቱ ክለቦች በቀጣዩ አመት ከሌሎች በተለያየ እርከን ላይ ካሉ 20 የአዲስ አበባ ክለቦች ጋር በመሆን የራሳቸውን ሊግ ሊመሰርቱ ሽር ጉድ ላይ እንዳሉም እየተነገረ ነው።
የባህር ማዶ ዜናዎች
✔️ናቾ ሞንሪያል ከአርሰናል ጋር ለተጨማሪ አምድ አመት የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።የ33 አመቱ ስፔናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ወደ ሀገሩ ክለቦች ሊመለስ እንደሆነ ሲነገር የቆየ ቢሆንም በስተመጨረሻ ለሰባተኛ ተከታታይ አመት ከመድፈኞቹ ጋር ለመሰንበት ከስምምነት ላይ ደርሷል።አርሰናል ይህንን የኮንትራት ማራዘሚያ ማምሻውን እንደሚያዳውቅ ይጠበቃል።
(THE SUN)
No comments:
Post a Comment