የዕለተ ሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች
አዘጋጅ-ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናል ከሁለት ተጨዋቾች ጋር በስፋት እየተነሳ ነው ዳኒ ሴባዮስን ከማድሪድ በውሰት ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው በማድሪድ እና በአርሰናል በኩል ያለው ልዩነት አሁንም በተጨዋቹ የውሰት ውል ላይ አርሰናል በማድሪድ ቤት የሚከፈለውን ሙሉ መክፈል አይፈልጉም ማድሪድ ደግሞ ከወሰዱት ሙሉውን ክፍያ እንዲከፍሉ ነግረዋቸዋል አርሰናል ሌላ አማራጭ ስለሌለው መስማማቱ ታውቋል የሜምፊስ ዴፓይ እና የማርቲት ዲሩን ወኪል ከኤስሚላን አለቆች ጋር ተገናኝቶ ተነጋግሩዋል ተብሏል ኤሲ ሚላን እነኚን ሆላንዳዊያንን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ፖውሎ ማልዲኒ ተናግረዋል
ትናንት የቀኝ መስመር ተከላካዩን ወደ አትሌቲኮ የሸኙት ቶተንሀሞች አሁን ደግሞ ሌላውን የግራ መስመር ተከላካዩን እንግሊዛዊውን ዳኒ ሮስን ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል ማንኛውም £25m ሚያቀርብ ክለብ ዳኒ ሮስን መውሰድ ይችላል ሮዝ ከእንግሊዝ ውጭ የመጫወት ምንም አይነት ፍላጎት የለውምም ተብሏል
ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር በግዳጅም ቢሆን ከፒኤስጂ ለመውጣት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ቀጥሏል ትናንት ማምሻውን እንደተሰማው ከሆነ ባርሴሎና ለልጁ ብሩን ከፍሎ የመግዛቱ ነገር ማይመስል የመሰለው ኔይማር ለሪያል ማድሪድ ማንችስተር ዩናይትድ ባይርን ሙኒክ ጁቬንቱስ ልታስፈርሙኝ ከፈለጋቹ ለናንተ ለመጫወት ዝግጁ ነኝ እንደሆነ ነግሮዋቸዋል
ኢንተሮች የሉካኩን ዝውውር ለማጠናቀቅ ቀናት ብቻ ቀርተዋቸዋል ለሱ ዝውውር ዩናይትድ የጠየቀውን ክፍያ ቦነስን ጨምሮ በአጠቃላይ እስከ 80ሚ.ዩሮ እንደሚያወጡ ለተጫዋቹ የነገሩት ሲሆን ይህም የሆነው አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቹን በጥብቅ ስለሚፈልገው ነው ተብሏል
አርሰናል እና ኮሸሌኒ ተፋጠዋል አርሰናል አሁን ኮሾሎኒን ከፍተኛ ገንዘብ ሊቀጣው በዝግጅት ላይ ይገኛል ኮሻ ወኪሉን ይዞ ነገ ከአርሰናል ሰዎች ጋር ተገናኝቶ እንደሚነጋገር ታውቋል
የቶተንሀሙ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ከቶተንሀም ለመውጣት ከጫፍ ደርሱዋል የጣሊያኑ ፊዮሬንቲና የልጁ ፈላጊ ሆኖ መቷል የ34 አመቱ አጥቂ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ለመግባት ከጫፍ መድረሱም ታውቋል
ለረጅም አመታት በሮማ የተጫወተው ዳኒኤሊ ዲሮሲ ወደ አርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየርስ ለቀጣይ ስምንት ወራት ለመጫወት ሊያመራ ከጫፍ ደርሷል እዛው ጣሊያን በመቆየት ለኤሲ ሚላን አልያም ለፊዮሬንቲና ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ሲጠበቅ በመጨረሻም ምርጫውን አርጀንቲና አድርጓል
የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ሲሞን ሚኞሌት በቀጣዩ አመት በቋሚነት የሚሰለፍበትን ክለብ መቀላቀል እንደሚፈልግ ወኪሉ አስታውቋል ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ግብ ጠባቂው በአንፊልድ እንዲቆይ አሁንም ፍላጎት አለው
No comments:
Post a Comment