የዕለተ ዓርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
የቀድሞ የሊቨርፑል እና አሁን ላይ ክለብ አልባ ሆኖ የተቀመጠው ዳኒኤል ስተሪጅ የሁለት ሳምንት የእግር ኳስ እገዳ ተጥሎበታል ይህም የሆነው የውርርድ ህግን በመተላለፉ ነው የእንግሊዝ እግር ኳስ ስድስት ሳምንት እገዳ ጥሎበት የነበረ ሲሆን ተከራክሮ ወደ ሁለት ሳምንት ዝቅ አስደርጓል
ክርሶቶፎር ኑኩንኩ ወደ ጀርመኑ አርቢ ላይብዢክ ማምራቱ ተረጋግጧል ፈረንሳዊው ወጣት በተለያዩ ክለቦች ቢፈለግም በመጨረሻ ጀርመን ሆኗል ማረፊያው በሌብዢክ አምስት አመት የሚቆይ ሲሆን ለዝውውሩ ለፒኤስጂ 13ሚዩ ከፍለዋል
ሪያል ማድሪድ ኢስኮን ለመሸጥ ፍላጎት አላቸው ባሳለፍነው አመት ብዙም በማድሪድ ደስተኛ ያልሆነው ኢስኮ በክረምቱ ማድሪድን ስለመልቀቅ ባያስብም ማድሪድ ግን ለኢስኮ የሚመጣን ዝውውር ለመስማት ዝግጁ ሆነዋል ለልጁም ማድሪድ እስከ 80ሚዩ ይፈልጋሉ
አትሌቲኮ ማድሪድ ማሪዮ ሄርሞሶን ከኢስፓኞል አስፈርሟል ዲያጎ ጎዲን እና ሉካ ሄርናንዴዝ ክለቡን መልቀቃቸውን ተከትሎ ተተኪ ተከላካዮችን እያገኙ ይገኛሉ ከቀናት በፊት እንግሊዛዊውን ትሪፔርን ማስፈረማቸው ይታወሳል በመሀል ተከላካይ እና በግራ መስመር ተከላካይ መጫወት ሚችል ሲሆን ሪያል ማድሪድ £7.5m ልጁን ማስፈረም ይፈልግ ነበር ግን በመጨረሻም አትሌቲኮን መርጧል
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ አሰልጣኝነታቸው ሊመለሱ ነው አምና ከዩናይትድ ከተሰናበቱ ቡሀላ ክለብ አልባ ሆነው የቆዩት ጆዜ ከምንም ጊዜ በላይ ወደ ስራቸው ለመመለስ ጓጉተዋል ወዴት እንደሚያመሩ ግልፅ ባይሆንም ወደ ጀርመን ሄደው ሊሰሩ እንደሚችሉ ተነግሯል ምክንያቱም ጆዜ ጀርመንኛ እየተማሩ ስለሚገኙ ነው የሚል መረጃ ወቷል
ፍሬድ ወደ ቱርክ ለማምራት ተቃርቧል የቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ፍሬድን በውሰት ለማስፈረም ከዩናይትድም ከልጁም ጋርም መስማማቱ ታውቋል የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ሮማ እንዲመጣላቸው ቢፈልጉም ልጁ ግን ወደ ጋላታሳራይ ለማምራት ተቃርቧል
የአድራን ራቢዮ እና የአሮን ራምሴ ቱሪን መድረስ ተከትሎ እና በቦታው ብዛት ያላቸው አማካዮች ያሉበት ፈረንሳዊው ኮከብ ብለስ ማቲዩዲ ክለቡን ለመልቀቅ ፍላጎት አለው ልጁን ለመውሰድ የቀድሞ ክለቡ ፒኤስጂ እና የእንግሊዞቹ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተኖች ፈላጊ ሆነው መተዋል
ሶሎሞን ሮንዶን ወደ ቻይናው ዴሊንግ ይፋንግ ለማምራት ተቃርቧል ምርመራውንም ትናንት አጠናቋል ውል ማፍረሻውም £16.5m ነበር ውል ማፍረሻውን ለመክፈል ተስማምቷል በድጋሚ በኒውካስትል አብሮት ከሰራው ራፋ ቤኒቴዝ ጋር ተገናኝቶ የመስራት እድል አግኝቷል
ኬራን ትሪፒየርን ለአትሌቲኮ አሳልፈው የሰጡት ቶተንሀሞች አሁን ደግሞ የግራ መስመሩን ዳኒ ሮስን ለመሸጥ አስበዋል ቶተንሀሞች ከ20-25ሚፓ ለሚያቀርብ ክለብ መሸጥ ይፈልጋሉ ካሁኑ ፈላጊ ክለቦች የመጡ ሲሆን የጀርመኑ ሻልካ04 እና የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ፈላጊዎቹ ናቸው ልጁ ግን እንግሊዝ ነው መቆየት ሚፈልገው
በብዙ የአውሮፓ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው የፉልሀሙ ጃን ሚሼልሴሪ በመጨረሻም ጋላታሳራይን ተቀላቅሏል በጋላታሳራይ ቀጣይ አመትን በውሰት የሚያሳልፍ ይሆናል
No comments:
Post a Comment