አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር(የሪሐና ልጅ)
ጁቬንትስ ፖግባን ለማስፈረም ሶስት ተጨዋቾችን ለዩናይትድ አቅርቧልበተከታታይ ሴሪ ኤውን በማሳካት የንግስናውን ዘውድ የደፋችው አሮጊቷ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን በቀጣዩ አመት ለመቀዳጀት ወጥና መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች።ለዚህም ይረዳ ዘንድ በርካታ ኮከቦችን በማስፈረም ላይ ስትሆን በዋናነት የቀድሞ ተጨዋቿን ፖል ፖግባ ትፈልጋለች።
ማውሪዚዮ ሳሪም የፈረንሳዊው አማካይ ቱሪን መምጣትን አጥብቀው ስለሚሹ የክለቡ የበላይ አመራሮች ይህንን የዝውውር ጉዳይ ከግብ ለማድረስ ደፋ ቀና ቢሉም ማን ዩናይትድ ግን የዋዛ ተደራዳሪ ሆኖ አልተገኘም ፥ መዘግየቱም ከዚህ የመጣ።
እንደ Corriere della Sera ዘገባ ከሆነ ጁቬንትስ ተጨዋቹን ለማዘዋወር እና በቀያይ ሰይጣኖቹ የተጠየቀውን £150M ገንዘብ ለመቀነስ ለእንግሊዙ ሐያል ክለብ ሶስት ተጨዋቾችን የዝውውሩ አካል አድርጎ ለመስጠት ጥያቄውን አቅርቧል።እነዚህም ተጨዋቾች ጁዋዎ ካንሴሎ፥ዳግላስ ኮስታ እና ብሌስ ማቲዉዲ ናቸው ብሏል ጋዜጣው በሀተታው።
ፖግባ አዲስ ፈተና እንደሚፈልግ እና ከቲያትር ኦፍ ድሪምስ መውጣትን እንደሚከጅል ከዚህ በፊት መናገሩ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment