Friday, July 19, 2019

የአርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

የአርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ-ኢብራሒም መሐመድ

አርሰናል ዊሊያም ሳሌባን ለማስፈረም በጣም ተቃርበዋል አርሰናል ክለቡ ሴንቲቲየን የጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል አርሰናል ለዘንድሮ የውድድር አመት ልጁን መገልገል አይችልም ምክንያቱም ልጁን በቀጣይ አመት በውሰት እዛው የሚቆይ ይሆናል አርሰናልም ለልጁ £29+ቦነስ የሚከፍል ይሆናል ዝውውሩ ለመጨረስም ከጫፍ ደርሷል



ባርሴሎና ኔይማርን ለማስፈረም £90 እና ተጨማሪ አንድ ተጨዋች በመስጠት ለመውሰድ አስበዋል ባርሳዎች ለፒኤስጂ ስድስት ተጨዋቾችን በአማራጭ አቅርበውላቸዋል ከነሱ ውስጥም ዴምቤሌ ኩቲንሆ እንደሚገኙበት ታውቋል ባርሳም ይፋዊ ጥያቄ እንዳቀረበ ታውቋል




ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉት አስቶንቪላዎች በረኛ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ፊታቸውንም ወደ በርንሌው ቶም ሂተን ፍላጎት አሳይተዋል ለልጁ እስከ £12m ያሶጣቸዋል ተብሏል




አጥቂ ለማስፈረም ወደ ገበያ የወጡት ዎልቨርሀምፕተን ወንድረሶች ፊታቸውን ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኤሲሚላን በማዞር ፓትሪክ ክሩቴኔን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል ለልጁ ሚላን £22m ይፈልጋሉ ዎልቭሶች ከሌሎች ክለቦች የተሻለ ልጁን የማስፈረምም እድል አላቸው





ዩናይትዶች ሉካኩ ክለቡን ሚለቅ ከሆነ እሱን እንዲተካላቸው የአርሰናሉን አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦቦምያንግን ለማስፈረም እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን ለተጫዋቹ ግዢ የሚሆን £62m እንዳዘጋጁም ተዘግቧል




አሮዋን ቢሳካን ለዩናይትድ አሳልፈው የሰጡት ክርስቲያል ፓላሶች ፊታቸውን ወደ አርሰናሉ ካርል ጄንኪክሰን አዙረዋል ልጁ በአርሰናል ብዙ የመሰለፍ እድል ማያገኘው ጄንኪክሰን ወደ ፓላስ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል




ቶተንሀሞች ኬራን ቴሪፒየርን ለመተካት ፊታቸውን ወደ ሁለት ተጨዋቾች አዙረዋል አሌሳንድሮ ፍሎሬንዚ ወይም  ኢልሴይድ ሂሳጅ ከሁለቱም አንዱን ማስፈረማቸው አይቀሬ ይመስላል




አዲስ አዳጊዎቹ ካርዲፍ ሲቲዎች የሚድልስቦሮ ተከላካይ የሆነውን አደን ፍሊንትን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሱዋል ካርዲፎች ለልጁ ለሚድልስቦሮ £6 ለመክፈል ከስምምነት ደርሰዋል




በአርሰናል በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ዊልፍሬድ ዘሀ ይፋዊ የልቀቁኝ ደብዳቤ ሊያስገባ መሆኑ ተሰምቷል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ትልቅ ክለብ መዘዋወር ፈልጋለው ብሎ መናገሩ የሚታወስ ይሆናል

1 comment:

  1. ፅሀፉ በጣም ደቀቀ
    ለማንበብ ያስቸግራል

    ReplyDelete

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...