የቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም መሐመድ
የቱርኩ ጋላታሳራይ ኮሎምቢያዊውን የሞናኮ አጥቂ ራዳሜል ፋልካዎን ለማስፈረም እየተደራደሩ ነው ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል በአመት 7ሚዩ እንደሚከፍሉት ነግረውታል በሞናኮ የአንድ አመት ኮንትራት ሚቀረው ፋልካኦ ወደ ጋላታሳራይ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል የቀድሞ ብራዚላዊው ኮከብ ሮናልዲንሆ ጉቾ በድጋሚ ወደ እግር ኳስ ሊመለስ ነው የ39 አመቱ ጉቾ በማላታ ፕሪሚየር ሊግ ሚጫወተው ቢርኪርካራFC ጋር እየተደራደረ ነው የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ማይክል ቫሌንሲያ እውነት ነው እየተደራደርን ነው ከሮናልዲንሆ ጋር ሚሆነውን እናያለን ብለዋል
የቀድሞ የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ቪክተር ቫልዴዝ በድጋሚ ወደቀድሞ ቤቱ ባርሴሎና ተመልሷል በባርሳ U-19 አሰልጣኝ ተደርጎ የተሾመ ሲሆን ስራውንም በይፋ ጀምሯል
ሪያል ማድሪድ ፖል ፖግባን ለማስፈረም ቆርጠው ተነስተዋል እስካሁን ለዩናይትድ ይፋዊ ጥያቄ ባያቀርቡም አሁን ግን ያሰቡት ከተሳካ ፖግባን ማስፈረም እንደሚችሉ ተማምነዋል ፖግባንም ወደ ቤርናቦ ለመውሰድ አምስት ተጨዋቾችን ለሽያጭ አቅርበዋል ከሽያጩ የሚገኘውንም ገቢ እስከ £200m የተጠየቁትን ፖግባን ለማስፈረም ፈልገዋል
ብዙ ጀርመናዊ የእግር ኳስ ሰዎች የሲቲው ሊዩሬ ሳኔ ላይ ከሲቲ እንዲለቅ ተፅኖ እያሳደሩበት ነው ብዙ ጊዜ ስሙ ከባየርን ሙኒክ ጋር እየተነሳ የሚገኘው ሳኔ በክረምቱ ወደ ሀገሩ ክለብ የመመለስ እድል አለው ከቀናት በፊት ፔፕ ጋርዲዮላ ሁሉም ተጨዋች በሲቲ ቤት በፍላጎት ብቻ እንዲቆይ ነው ምፈልገው ማለቱ ይታወሳል ይሄም ለሳኔ አንድ መውጫ ቀዳዳ ከፍቶለታል
በጁቬንቱስ የመቆየቱ ነገር ሚያጠራጥረው ጎንዛሎ ሂግዌን ጁቬን ለቆ ወደ ጣሊያኑ ሮማ እንዲያመራ አረንጓዴ መብራት በርቶለታል ልጁ በቱሪን መቆየት ቢፈልግም ክለቡ ግን በክረምቱ እንደሚለቁት ተረጋግጧል
ወደ ቻምፒዮን ሺፑ የወረዱት የዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ፉልሀሞች ከፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ብራይተን ሆብአልቢዮን የመስመር ተጨዋች የሆነውን አንቶኒ ክኖካሬት ለማስፈረም ተቃርበዋል ለተጨዋቹ ፉልሀሞች £15m የከፈሉ ሲሆን ትናንት ማምሻውን በፉልሀም የህክምና ምርመራውን አከናውኗል
በሮሜሉ ሉካኩ ቆይታ ላይ እርግጠኛ ያልሆኑት ዩናይትዶች ከተለያዩ ክለቦች የፊት መስመር አጥቂዎች ጋር ስማቸው
ሲያያዝ ቆይቷል አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ጁቬንቱሱ አጥቂ ፖብሎ ዲባላ አዙረዋል ዲባላን ለማስፈረም ዩናይትዶች ሰዎቻቸውን ወደ ጣሊያን ልከዋል ተጫዋቹም እስከ 80ሚዩ ነው የተገመተው
No comments:
Post a Comment