የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
አቅራቢ-ኢብራሒም ሙሐመድ
ባርሴሎና ለኔይማር ዝውውር ኢቫን ራኪቲች + ፊሊፕ ኩቲንሆ + £40m አቅርቦ በፒኤስጂ ውድቅ እንደተደረገበት ታማኙ የፈረንሳይ ጋዜጣ ሌኪፕ አስነብቧል ፒኤስጂዎች ግን አሁንም እስከ 222ሚዩ ነው ከዝውውሩ የሚፈልጉትአዲሱ የሮማ አሰልጣኝ ፎንሴካ ከቀድሞ የሻካታር ልጃቸው ከዩናይትዱ ፍሬድ ጋር ድጋሚ በሮማ ለማስፈረም እንደሚፈልጉ እና ወደ ሮማ እንዲመጣ ጥያቄ አቅርበዋል ነገር ግን ኦሌ በቀጣይ አመት እቅዳቸው ውስጥ እንዳለ ነግረውታል
ኤሲ ሚላን ክሮሺያዊውን ኮከብ ሉካ ሞድሪችን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል ነገር ግን ሉካ ሞድሪችም በክለቡ መቆየት ይፈልጋል ዚዳንም እንዲለቅ አይፈልግም
ኬረን ቲሪፔርን ለአትሌቲኮ አሳልፈው የሰጡት ቶተንሀሞች አሁን ደሞ ሌላኛውን የቀኝ መስመር ተከላካያቸውን ሰርጂ ኦሬርን ለመልቀቅ አስበዋል ይህን ተከትሎ ከፈረንሳይ የማርሴውን ሂሮኪ ሂሳካዬን ወደ ሰሜን ለንደን የማምጣት ፍላጎት አለው
አርሰናሎች የሪያል ማድሪዱን ዳኒ ሴባዮስን ዝውውር ለመጨረስ ከጫፍ ደርሰዋል በቶተንሀም በጥብቅ ቢፈለግም ወደ አርሰናል ለመግባት ተቃርቧል አሁን የሚጠበቀው የዚዳን ፍቃድ ብቻ ነው
ከአንድ አመት የውሰት ውል ቆይታ ቡሀላ ወደ ጁቬንቱስ የተመለሰው ጎንዛሎ ሂግዌን ከጁቬንቱስ እንዲወጣ እንደሚፈለግ ታውቋል ክለቡ ወደ ሮማ እንዲሄድ ይፈልጋል እሱ ደግሞ ከጁቬንቱስ መልቀቅ አይፈልግም ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጥያቄዎች እየቀረቡለት ነው ኤቨርተን እና ዌስትሀምም ተጨዋቹን በውሰት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው
ዌስትሀም ዩናይትድ የክለቡን ክብረወሰን አሻሽሎ ፈረንሳዊውን አጥቂ ሴባስቲያን አለርን ከቦሩሲያ ሞንቼግላድባ በ£45m አስፈርሟል ባሳለፍነው የውድድር አመት በቡንደስሊጋው 15ግቦችን በኢሮፓ ሊግ 5 ግቦችን አስቆጥሯል ልጁ በዩናይትድም በጥብቅ ይፈለግ ነበር
የሊሊያም ቱራም ማርከስ ቱራም ኪከር እንዳለው ወደ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባ ለመዘዋወር ተቃርቧል ይህ ማለት ደግሞ የሴባስቲያን አለርን ምትክ ሆኖ ነው ሚዘዋወረው የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ልጁን ለማስፈረም ጥሩ ተስፋ አለን ብለዋል ከ10 እስከ 12 ሚዩ ያወጣል ተብሏል
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ከሆነ አርሰናል ዊሊያን ሳሊባ ሚባለውን ተጨዋች ለማስፈረም ከቶተንሀም ሳያሸንፉ እንዳልቀሩ ተሰምቷል የሴንቲቲያኑ ተከላካይ በቀጣይ አመት እዛው በክለቡ ይቆይ እና በ2020/2021 የውድድር አመት ነው ለአርሰናል ግልጋሎት መስጠት ሚጀምረው £27m ወጪ አድርጓል ልጁ ከቶተንሀም ይልቅ አርሰናል መርጧል
ሪያል ማድሪዶች በመጨረሻም በይፋ ጋሪዝ ቤልን ለመሸጥ ዋጋ ለጥፈውበታል ማድሪዶች ማንኛውም 80ሚዩ ሚያቀርብ ክለብ ከመጣ ልጁን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሆነዋል ተጨዋቹ በማድሪድ መቆየት ቢፈልግም ማድሪዶች ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ ስላወጡ እሱን በመሸጥ ማካካስ ይፈልጋሉ
No comments:
Post a Comment