Monday, June 17, 2019

ባርሳ ኔይማርን ለመመለስ ድርድር እያደረገ ነው

ባርሳ ኔይማርን ለመመለስ ድርድር እያደረገ ነው
አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ብራዚላዊው አጥቂ ድራማዊ በሆነ መልኩ ወደ ካታሎኒያ ሊመለስ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
Globoesporte እንደዘገበው ባርሴሎና ከክለቡ ፓሪሰም ዤርመን ጋር የ27 አመቱን አጥቂ በማስፈረም ጉዳይ ላይ ድርድር ጀምሯል።ኔይማር የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ አንስቶ ስሙ በስፋት ከተለያዩ ሀያል የአውሮፓ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ሲሆን ወደ ብሉግራናዎቹ ይሄዳል የሚለው ዜና ግን ሚዛን እየደፋ ይመስላል።

ጋዜጣው እንደዘገበው ባርሳ ያቀረበው €100ሚ. ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ ሳሚኤል ኡምቲቲ ፥ ኦስማን ዴምቤሌ እና ኢቫን ራኪቲችም የዝውውር አካል እንዲሆኑ ይፈልጋል።


ትናንት ከኔይማር ጋር በተያያዘ ጥያቄ የቀረበለት የቀድሞው የክለብ አጋሩ ሊውስ ሱዋሬዝ "ማን ነው ኔይማርን የማይፈልገው ክለብ?" በማለት ተጨዋቹ በሁሉም ክለቦች የሚፈለግ ትልቅ ተጨዋች መሆኑን ተናግሮ ወደ ካምፕ ኑ ቢመጣ እንደሚደሰት ተናግሯል።
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴ ደግሞ "ኔይማር መጫወት ያለበት የሚያስደስተው ክለብ ውስጥ ነው" በማለት ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...